አብሮ አደጎቹ የ91 እና የ92 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ አባቶች በተመሳሳይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል

ሸገር ልዩ ወሬ – SHEGER FM 102.1 RADIO

 

አብሮ አደጎቹ የ91 እና የ92 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ አባቶች በተመሳሳይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል…

በ1920 የተወለዱት ሊቀጠበብት ቀፀላ አምበርብር እና በ1921 የተወለዱት ቀኝ ጌታ ብርሃኑ መኩሪያ አብሮ አደጎች ናቸው፡፡ በአብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥም በአንድ ጎጆ ለዓመታት ኖረዋል፡፡ በመንፈሳዊ አገልግሎትም አልተለያዩም፡፡ ሁለቱም እያንዳንዳቸው የ6 ሴቶች እና የ3 ወንዶች ልጆች ወላጅ ናቸው፡፡

የሚዋደዱት አብሮ አደግ አባቶች በአንድ ቀን፣ በተመሳሳይ ሰዓት ከዚህ ዓለም መለየት እና የሕይወት ታሪካቸው በጋራ ተነብቦ በአንድ ጉድጓድ መቀበር የገብረ ጉራቻ/ኩዩን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ወሬውን የሰማውን ሁሉ አጀብ አስብሏል፡፡