የጤፍ ዋጋ መናርና የስንዴ ዱቄት እጥረት ስጋት አሳድሮአል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑ ተነገረ። ነዋሪዎች እንደሚሉት የጤፍ ዋጋ ንሯል። አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ 3 ሺህ 500 ብር ደርሶአል።

የስንዴ ዱቄት እጥረት በመከሰቱም የዳቦ ቤቶች አቅርቦት ዉስን መሆኑ እየተነገረ ነዉ። የጤፍ ዋጋ ላለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ምንም ጭማሪ ያላሳየ ቢሆንም ፤ ይሁንና በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ከ 2 ሺህ 800 እስከ 3 ሺህ 300 እና 3 ሺህ 500 ብር ድረስ መግባቱ ስጋት አሳድሮአል።

ከጤፍና ከስንዴ ሌላ የዳቦ የእንጀራ እንዲሁም ሽንኩርትን የመሳሰሉ መሰረታዎ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ ተገልፆአል።

DW Amharic

Image may contain: food and indoor