6 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዘጉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከህግ ውጪ ሲያተምሩ የተገኙ 6 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዘጉ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህግን ተከትለው ስለመንቀሳቀሳቸው ለማረጋገጥና ከስነ ስርዓት ውጪ የሆኑትን ወደ መስመር ለማስገባት ሲባል የከፍተኛ ጥራት እና አግባብነት ኤጀንሲ በ25 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ጉብኝት ህግ ተላልፈው ተገኙ ባላቸው 6 የግል ከፍተኛ ተቋማት ላይ እንዲዘጉ እርምጃ መውሰዱን ለጣቢያችን አታውቋል፡፡

ከነዚህ መካከል ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ካምፓስ፣ ኢትዮ ስማርት ኮሌጅ አድዋ ካምፓስ እና በጋምቤላ ከተማ 4 ተቋማት ማለትም ላትጆር ኮሌጅ፣ዌስተርን መካኢየሱስ ኮሌጅ፣ ሾውቤል ኮሌጅ እና ሉተራን ካቶሊክ ኮሌጅ ይገኙበታል ሲል ኤጀንሲው ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡

ተቋማቱ በሚሰጧቸው ፕሮግራሞች ላይ የእውቅና ፍቃድ ሳያገኙ እንዲሁም ተቀብለው እንዲያስተምሩ ከተፈቀደላቸው የተማሪዎች ቁጥር በላይ ተቀብለው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ደረጃ ሲያተምሩ የተገኙ ናቸው፡፡

ተቋማቱ ሲዘጉም ህጋዊ ተማሪዎች ህጋዊ ወደ ሆነ ሌላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንዲዛወሩ መደረጉንም ኤጅሲው አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በ6 ከተሞች የሚገኙ 17 ካምፓሶች ላይ ድንገተኛ ጉብኝት ተደርጎ ከህግ ውጪ ሲያስተምሩ በመገኘታቸው በቀጣይ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ኤጀንሲው ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡

Source : ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8