መንግስታዊ ህገወጥነት ምን ሊያመጣ እንደሚችል እናጢን !!!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መንግስታዊ ህገወጥነት ምን ሊያመጣ እንደሚችል እናጢን !!!
አፉን ያለልክ የሚከፍት የማንም ሰው ዕጣ-ፈንታ የአድማጩ ሰለባ ይሆናል !!! ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
 
የምናስባቸውንም የምንጠረጥራቸውንም ጉዳዮች ሁሉ አስቀድመን በተግባር እናረጋግጥ፡፡ በማናቸውም መልኩ በወሬ አንፈታ! ከመፎከርም ከማውራትም በተግባር ምን እናድርግ? ማለት ተመራጭ ነው!! መረጃ መስጠት እንዳለ ሁሉ አሳሳች መረጃ መስጠትም አለ፤ አስቦ መጓዝ ይሄኔ ነው!በሁሉም ወገን የወሬ ናዳ አለ፡፡ ያ ወሬ እውነትም ይሁን ውሸት ህዝቡን ይፈታዋል፡፡በምንም ተአምር አትታለሉ፤ በማናቸውም መልኩ በወሬ አንፈታ!
 
የቤት-ሥራችንን ጠንቅቀን በመስራትና ጉዳያችንን በማወቅ ነው ለውጥ ለማምጣት የምንችለው፡፡ከሁሉም በላይ እብሪት አገርንና ህዝብን ይጐዳል፡፡ ከማንም በላይ ነኝ እና አምባገነንነት የእብሪት ልጆች ናቸው፡፡ ንቀት፣ ሰው-ጤፉነት፣ ሁሉን አውቃለሁ ባይነት፣ ቆይ-አሳይሃለሁ – ባይነት፤ ብቆጣም እመታሻለሁ ብትቆጪም እመታሻለሁ ማለት፤ከልክ ያለፈ ውዳሴና ማሞካሸትም ከጥቅሙ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው፡፡ ወረራ ዘረፋ የግልጽ ሽብር የትም አያደርስም ቀን የመጣ እለት ውርደት ራሱ አግጥጦ ይወጣል::ተወዳሹ እስኪታዘበን ድረስ ብናሳቅለው ለማንም የማይበጅ ተግባር እንደፈጸምን አደባባዮች ይመሰክራሉ፡፡
 
መንግስታዊ ህገወጥነት ምን ሊያመጣ እንደሚችል እናጢን፡፡ “እዛም ቤት እሳት አለ” የሚለውን ተረት ከልቦናችን አንለይ፡፡ ከቶውንም እኔ አውቃለሁን ስንፈክር ሌላውም ያውቃልን አንርሳ፡፡ ባደባንበት ሊደባብን እንደሚችል፣ ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን መሆኑን፣ ሥራ ለሰሪው እሾክ ላጣሪው እንደሚሆን አንዘንጋ፡፡አፉን ያለልክ የሚከፍት የማንም ሰው ዕጣ-ፈንታ የአድማጩ ሰለባ ይሆናል:: የሚለውን መዘንጋት የለብንም:: የህዝቦችን አመኔታ ለማግኘት መደማመጥ መከባበር መተባበር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም::