መንግስት ሕግ ለማስከበር ስርዓት አልበኞችን ለማስወገድ በቅድሚያ የራሱ መዋቅር ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት።

መንግስት ሕግ ለማስከበር ስርዓት አልበኞችን ለማስወገድ በቅድሚያ የራሱ መዋቅር ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት።

የመንግስት ዝምታ ወንጀለኞቹን እያበረታታ ሲሆን በጦር ሰራዊቱና በፖሊሱ ውስጥ ስርዓት አልበኝነትን እንዳያስፋፋ ስጋት አለ። መንግስት መዋቅሮቹን ስላዝረከረከ አቅመ ቢስ ሆኗል። መንግስት ተቋማቱንና መዋቅሮቹን ቢያጠነክር የዜጎችን ሰላምና ደሕንነት ማረጋገጥ አያቅተውም።

የሐይማኖት ተቋማትን ከሐረርጌ እስከ ጎጃም ሞጣ እያቃጠሉ ያሉት እኮ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የፀጥታና የደሕንነት ተቋማትን የሚመሩ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና አዛዦቻቸው እነጃዋርና የመቀሌ ከበርቴዎች ሕወሓቶች ናቸው።

ዱርዬዎችን በገንዘብ ከመግዛት አንስቶ ከባድ ሽብር የሚፈጽሙትን የሚያደራጁ የሚመሩ እቅድ የሚነድፉ ወዘተ እነማን ይህን ጥፋት እንደሚፈጽሙ መንግስት በቂ የደሕንነት መረጃዎች አሉት።

የሕዝብን ሰላም እና ደሕንነት ማረጋገጥ የሚቻለው ለወታደራዊ መኮንኖችና ለማይረቡ የዩንቨርስቲ መምሕራኖች የማእረግ እድገት በመስጠት አይደለም። የመንግስት መዋቅር በአወናባጆችና በሰላም አደፍራሾች የተሞላ ነው።

መንግስት በራሱ ላይ እሳት ለኩሶ እየተለበለበ ነው።ማጥፋት እየቻለ ስንፍና አቅመቢስ አድርጎታል። መፍትሔው መዋቅሩን መቀየርና በጠንካራ መሰረት ላይ ተቋማትን መገንባት ብቻ ነው። #MinilikSalsawi