ቆራጡና ጽኑው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ታላቅ የምስጋና ዝግጅት ተካሄደለት

ከህወሃት የሚደርሰበት እስር፣ሰቆቃና መከራ ሳይበግረው ለኢትዮጵያ ህዝብ የገባውን ቃል አክብሮ በጽናት፣በትጋትና በቁርጠኝነት የጋዜጠኝነት ሙያውን በመወጣቱ ምክንያት ለበርካታ ዓመታት በእስር ሲሰቃይ የነበረውና በቅርቡ የተለቀቀው እስክንደር ነጋን የማመስገኛ ዝግጅት በዛሬው ዕለት አሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ ውስጥ ተካሄዷል። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊን ከመሳተፋቸውም በላይ ዝግጅቱ የተካሄደበት አዳራሽ ከአፍ እስከገድፉ በመሙላቱ ሳይሳተፉ የተመለሱም በርካቶች ናቸው።ዝግጅቱ እጅግ ያማረና የሰመረ እንዲሁም የሞቀና የደመቀ ነበር።ከዚህም በተጨማሪ የአሌክሳንደሪያ ከተማ ከንቲባና የጋዜጠኞች መብት አስከባሪ ድርጅቶች ተወካዮችም ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። ስለዝግጅቱ የተጠናቀረ ዝርዝር ዘገባ እናስከትላለን።