ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች የማዕረግ ሹመት ተሰጠ – (የሹመቱን ዝርዝር ይዘናል)

ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች የማዕረግ ሹመት የመስጠት ስነ ስርዓት ተከናወነ

(ኤፍ ቢ ሲ) ፦ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዣዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት በኢፊዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የማዕረግ ሹመቱ ተሰጠ ።

በኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከብርጋዴር ጀኔራል እስከ ሌተናል ጀኔራል ማዕረግ የተሰጣቸው 65 የኢፌዴሪ መከላከያ መኮንኖች
**************************************

ከሜ/ጀኔራል ወደ ሌ/ጀኔራል ማዕረግ የተሾሙ፤-
1. ሜ/ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ ፈንታ
2. ሜ/ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና
3. ሜ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን
4. ሜ/ጄኔራል ይመር መኮንን
5. ሜ/ጄኔራል ደስታ አብቼ
6. ሜ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

ከብ/ጄኔራል ወደ ሜ/ጄኔራል ማዕረግ የተሾሙ፤-
1. ብ/ጄኔራል ገ/መድህን ፍቃደን ኃይሉ
2. ብ/ጄኔራል ኩመራ ነገሪ ገመዳ
3. ብ/ጄኔራል ከድር አራርሳ ይመር
4. ብ/ጄኔራል አሰፋ ቸኮለ እንዳለው
5. ብ/ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ አብተው
6. ብ/ጄኔራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን ደጋ
7. ብ/ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ለሙ
8. ብ/ጄኔራል ሀብታሙ ጥላሁን ሄስቤቶ
9. ብ/ጄኔራል ታደሰ መኩሪያ ዘሪሁን
10. ብ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ኛጳ
11. ብ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ ተገኝ
12. ብ/ጄኔራል ይርዳው ገ/መድህን ገ/ፃድቅ
13. ብ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በዳዳ
14. ብ/ጄኔራል ሙዘይ መኮንን ተወልደ
15. ብ/ጄኔራል ነጋሲ ትኩዕ ለውጠ
16. ብ/ጄኔራል ተሾመ ገመቹ አደሬ
17. ብ/ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ ገ/ኪዳን
18. ብ/ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ አበራ
19. ብ/ጄኔራል አህመድ ሀምዛ

ከኮሎኔል ወደ ብ/ጀኔራል ማዕረግ የተሾሙ፤-
1. ኮሎኔል አሊጋዝ ገብሬ በርሄ
2. ኮሎኔል ጎይቶም ፋሩስ በላይ
3. ኮሎኔል አብረሃ መውጫ በየነ
4. ኮሎኔል ፍትዊ ፀሃዬ ገ/እግዚአቤር
5. ኮሎኔል ይልማ ከበደ ገ/መስቀል
6. ኮሎኔል ጠቅለው ክብረት ይመር
7. ኮሎኔል አብዱሰላም ኢብራሂም ሙሳ
8. ኮሎኔል ዘውዱ ሰጥአርጌ ደነቀ
9. ኮሎኔል መሸሻ አረዳ ሂርጶ
10. ኮሎኔል ሻምበል ፈረደ ውቤ
11. ኮሎኔል ኩማ ሚደቅሳ ሰንበታ
12. ኮሎኔል ሙስጠፋ መሃመድ አብዲ
13. ኮሎኔል አበበ ተካ ወ/ሩፋዮል
14. ኮሎኔል ሚልኬሳ ረጋሳ ኢተፋ
15. ኮሎኔል ግዛው ኡማ አብዲ
16. ኮሎኔል አብድሮ ከድር በናታ
17. ኮሎኔል መለስ መንግስቴ ንረይ
18. ኮሎኔል መለስ ይግዛው መድፉ
19. ኮሎኔል ያሲን መሃመድ ሲሳይ
20. ኮሎኔል አብደላ መሃመድ ተገኝ
21. ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው አለሙ
22. ኮሎኔል ይታያል ገላው ቢተው
23. ኮሎኔል ሙሉጌታ አምባቸው ጎሹ
24. ኮሎኔል ተስፋዬ ረጋሳ አመንቴ
25. ኮሎኔል ነገሪ ቶሊና ጉደር
26. ኮሎኔል ጡምሲዶ ፈታሞ ዱባለ
27. ኮሎኔል ፍስሃ ገ/ስላሴ እኑን
28. ኮሎኔል በርሄ ገ/መድህን ደመወዝ
29. ኮሎኔል ናስር አባዲጋ አባዲኮ
30. ኮሎኔል ተመስገን አቦሴ ዳቴቦ
31. ኮሎኔል ወርቁ ከበደ ወልደየሱስ
32. ኮሎኔል እናሶ ኢጃጆ አናሾ
33. ኮሎኔል ደረጀ መገርሳ ኢሰታ
34. ኮሎኔል ነገራ ለሊሳ ሙለታ
35. ኮሎኔል ሰብስቤ ዱባ ኡንቲሶ
36. ኮሎኔል ዘላለም ፈተና ቀቀሞ
37. ኮሎኔል ዋለፃ ዋቻ ዋራ
38. ኮሎኔል የሺእመቤት አያሌው
39. ኮሎኔል እርጎ ሺበሺ ሲሳይ
40. ኮሎኔል ሸዋዬ ኃይሌ

የማዕረግ ሹመት አሰጣጡ ላይ ንግግር ያደረጉት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ “በሀገሩ የሚኮራ፤ ሀገሩን የሚያኮራ፤ ለዘመናት ጀግንነቱን ያስመሰከረ፤ ድል ማድረግ ዜማው ፤ ማሸነፍ ቋንቋው የሆነ፤ የራሱን የማይሰጥ የሰውን የማይወስድ እንዲሁም ሰላምን ከፍ ለማድረግ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ” ብለውታል የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊትን።

መከላከያ ሰራዊቱ በውስጥ ሰላምና ደህንነትን በውጪ ድንበርና ሉዓላዊነትን እያስከበረ ይገኛል ብለዋል የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዣዡ።

ከድሆች ጓዳ እስከ ገበሬው አጨዳ ተሰማርቶም የሚገኝ ጀግና ሰራዊት መሆኑንም አንስተዋል።

ምትክ ለሌላት ሀገራቸው ግንባራቸውን የሚሰጡ ጅግኖችን ሀገሪቱ ማፍራት ቀጥላለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ዛሬም ለሹመት የበቁት ወታደራዊ አመራሮች ለዚህ አብነት መሆናቸውን አንስተዋል።

በዛሬው ወታዳራዊ ሹመት አሰጣጥ የሴቶችን አኩልነት ለማሳደግ ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ሴት ወታደራዊ አመራሮች ሹመት እንደተሰጣቸውም ተናግርዋል። ወታዳራዊ ሹመቱም ተዋፅዕዎን የጠበቀ መሆኑንም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው መከላከያ ሰራዊቱ የሚቆመው ለህገ መንግስቱ መርሆች መከበር ብቻ መሆኑን በማንሳት ሁሉንም በእኩልነት ነፃ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

ሰራዊቱ የብሄረሰብም የሃሳብም ብዝሃነት እንዳለ አውቆ ከፓለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መቆም የሚችል መሆን አለበትም ነው ያሉት።

ማንኛውም ነገር ከሀገር ሉዓላዊነት አይበልጥም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የፓለቲካ ሀይሎች ህገ መንግስቱን አክብረው መንቀሳቀስ ግዴታቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ጀነራል መኮነኖች በውሏቸውና በስራቸው እንደሚመዘኑ በማንሳትም ውሏቸውና ስራቸውን እንዲያሳምሩ አሳስበዋል።