ከ1300 ሲሲ በታች ላሉ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች የሚጣለውን የረቂቁ የኤክሳይዝ ታክስ መጠን ከ 30% ወደ 5% ወረደ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከ1 ሺህ 300 ሲ ሲ በታች በሆኑ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚጣለው የታክስ መጠን ወደ 5 እንዲቀንስ ተደረገ

ረቂቁ የኤክሳይዝ ታክስ ከ1300 ሲሲ በታች ላሉ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች የሚጣለውን የታክስ መጠን ከ 30% ወደ 5% አወረደ:: ይህም የአዳዲስ ቤት መኪኖችን ዋጋ እስከ 83% ይቀንሰዋል ተብሏል።

(ኤፍ ቢ ሲ) ማሻሻያ በተደረገበት ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ በአዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚጣለውን የታክስ መጠን ከ30 በመቶ ወደ 5 እንዲቀንስ ተደረገ።

የገንዘብ ሚኒስቴር በተሻሻለው የኤክሳይዝ ታክስ ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በተሻሻለው ረቂቅ ከ1 ሺህ 300 ሲሲ በታች ባሉ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚጣለውን የታክስ መጠን ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ መውረዱን ገልጸዋል።

ይህም የተሽከርካሪዎችን ዋጋ እስከ 83 በመቶ ይቀንሰዋል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በሲጋራ እና አልኮል መጠጥ ላይ እንዲጣል የቀረበው ሃሳብ አነስተኛ ነው የሚል አስተያየት መቅረቡን ጠቅሰው፥ የመጠጥ ኢንዱስትሪው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲጋራ ላይ ብቻ ማስተካከያ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በዚህም በሲጋራ ላይ ተጥሎ የነበረው የ35 በመቶ ታክስ ወደ 36 በመቶ ከፍ እንዲል በማሻሻያው መቅረቡን ጠቅሰዋል።