በደህንነት ስጋት ከ35 ሺህ በላይ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ተባለ

(ኤፍ ቢ ሲ) ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በደህንነት ስጋት የወጡ ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈጠሩ ችግሮችን እንዲመረምር የተቋቋመው ኮሚቴ በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ያደረገውን የክትትልና የድጋፍ ሪፖርት አቅርቧል።

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተደረገው የኮሚቴው ምርመራ፥ 85 በመቶ ውጤታማ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ገልጸዋል።

የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተፈጠሩ ችግሮች ጋር ግንኙነት አላቸው ባሏቸው ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል።

በዚህም ወሎ ዩኒቨርሲቱ በ335 ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ እርምጃ ወስዷል።

ከዚህ ባለፈም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም የመማር ማስተማሩን ሂደት አውከዋል ባላቸው 18 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን መግለጹ አይዘነጋም።

በተጨማሪም ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ በ77 እንዲሁም ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ51 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውም የሚታወስ ነው።

እርምጃዎቹ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ማሰናበት የደረሱ ናቸው።

No photo description available.