" /> አሜሪካ በኢራን ላይ ልትወስደዉ የምትችለዉ ማንኛዉም የሀይል እርምጃ በመጀመሪያ በሴኔቱ ጉባኤ መጽደቅ አለበት ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

አሜሪካ በኢራን ላይ ልትወስደዉ የምትችለዉ ማንኛዉም የሀይል እርምጃ በመጀመሪያ በሴኔቱ ጉባኤ መጽደቅ አለበት ተባለ

The House votes to restrain Trump’s ability to use military action against Iran without congressional approval cnn.it/39T6c65

የአሜሪካ ሴኔት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚያራምዱትን ጦርነት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ የሚገድብ ዉሳኔ አሳለፈ፡፡ ሴኔቱ ዉሳኔዉን ያሳለፈዉ ትራምፕ ወደ ጦርነት ላለመግባታቸዉ ዋስትና እና እምነት በማጣቱ ነዉ ተብሏል፡፡ ዉሳኔዉ አሜሪካ በኢራን ላይ ልትወስደዉ የምትችለዉ ማንኛዉም የሀይል እርምጃ በመጀመሪያ በሴኔቱ ጉባኤ መጽደቅ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ በአሜሪካ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ ብቻ ራስን ለመከላከል የሚደረግ ቀለል ያሉ የማጥቃት እርምጃዎችን ብቻ እንዲወስኑ ትንሽ ስልጣን ብቻ ይሰጣል፡፡

ከዚህ ዉጭ ትራምፕ ከኮንግረንሱ ፈቃድ ዉጭ የአሜሪካን የጦር ሃይል በኢራን ላይ ለጥቃት በፈለጋቸዉ ሰዓት እንዳያዝዙም በትናንትናዉ እለት ገደብ ጥሏል፡፡ ኮንግረንሱ የ1973ቱ ዋር ፓዌር አክት ሰነድም መነሻ በማድረግ ሲሆን ዉሳኔዉን ያሳለፈዉ፣ ሰነዱ አሜሪካን ወደ ጦርነት ሊያስገባት የሚችል ሁኔታ ሲፈጠር ኮንግረንሱ ፕሬዝዳንቱን እንዲከታተልና በወታደራዊ ትዕዛዞች ላይ ያለዉን መብት በመጠኑም ቢሆን ለመገደብ የሚያስችል መብት የሚያጎናጽፍ እንደሆነ CNN ዘግቧል።


የመረጃ ቲቪ አባል ይሁኑ - JOIN US