የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከብልጽግና ፓርቲ የአባልነት ጥያቄ እንዳልቀረበለት ታወቀ

ከብልጽግና ፓርቲ የአባልነት ጥያቄ እንዳልቀረበለት የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፓርቲዎች በጋራ ስራቸውን፣ የገጠማቸውን ችግር እና የቀጣይ ስራዎች ዙሪያ በወር አንድ ጊዜ እየተገናኙ የሚመክሩበት ምክር ቤት ነው።ይህ ምክር ቤት ሲቋቋምና የቃል ኪዳን ፊርማ ሲፈረም የቀድሞ የገዥው ፓርቲን ኢህአዲግን በመወከል ፊርማቸውን ያኑሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነበሩ፡፡

በወቅቱም ይህ የጋራ ምክር ቤት ትልቅ ሀላፊነት ያለበትና እምነት የሚጣልበት የፖለቲካ ምህዳሮችን የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆነ ተናግረው ነበር ፡፡መንግስትም ድጋፍ እንደሚደርግም ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም አሁን ድረስ የፋይናስ ችግር ጨምሮ የመገልገያ ቁሳቁስ እጥረት እግር ከወርች አስሮታል ይላሉ የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሰቢ አቶ ግርማ በቀለ፡፡

ኢህአዲግ በይፋ መፈረሱንና አባል ድርጅቱቹ የብልጽግና ፓርቲን መስረተናል ማለታቸውን ተከትሎ የኢህአዲግ መስራችና ቀንደኛ ዘዋሪ የነበረው ህወሃት ብልጽግና ፓርቲን ጥገኛና አፍራሽ ሲል ገልጾ አብሮ እንደማይሰራ እና እንደማይዋሀድም ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡በአብሮነት ቆይታችን ካፈራነው ሃብት ድርሻዬን አስልታችሁ ስጡኝም ብሏል፡፡

ይህ መሰል ጥያቂ እንደቀረበለት የጠየቅነው የጋራ ምክር ቤቱ የአባልነት ጥያቄ አልወሃድም ካለው ከህወሃትም ሆነ ከብልጽግና ፓርቲ ጥያቂ አልቀረበልንም ብለዋል፡፡

ETHIO FM 107.8