ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በአሜሪካ የጦር መንደር ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ ውድቀቷ እየታየ ነው አሉ

President Trump says Iran “appears to be standing down” and no Americans were harmed in the attack on bases housing US troops in Iraq

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በአሜሪካ የጦር መንደር ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ ውድቀቷ እየታየ ነው ሲሉ ገለፁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር መንደር ላይ የፈፀመችውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካም ሆነ የኢራቅ ወታደሮች ህይወት እንዳላለፈ የገለፁ ሲሆን በጦር መንደሩ ላይ በተፈፀመው ጥቃት የተወሰነ ጉዳት ብቻ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ በመግለጫቸው አሜሪካ በኢራን ላይ በቀጥታ ተጨማሪ የፋይናስ እና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ልትጥል እንደምትችል በመግለፅ ይህም ባህሪዋ እስካልተቀየረ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊት ፕሬዚዳንቱ ኢራን የአሜሪካ የጦር መንደሮችን እና ወታደሮች ላይ ኢላማ ካደረገች ወታደራዊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠንቅቀው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ከዚህ አይነት አስተያየት መቆጠባቸው ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንቱ ኢራን የኒውክሌር ጦር ባለቤት እንዳትሆን እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

President Trump says Iran “appears to be standing down” and no Americans were harmed in the attack on bases housing US troops in Iraq