በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ምንም ዓይነት የግንኙነት መቀዛቀዝ የለም – የኤርትራ ፕሬዝዳንት

የጥላቻ ግንብን በመናድ የጀመረነው ትብብርና አብሮነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አቶ ኢሳያስ አፈውሪቂ የኤርትራ ፕሬዝዳንት

በሁለተኛ ሀገራችው ኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈውሪቂ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ተለያዩ የልማት ሥራዎችን የተመለከቱ ሲሆን ከመስክ መልስ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ካቢናችው ጋር በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ዝርዝርና ጥልቅ ምክክር ያደረጉ ሲሆን የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫውም የኤርትራናየኢትዮጵያ ህዝብ ለህዝብ እና በመንግስት ደረጃ የተጀመረው ሰላማዊ ግንኙነት ሃያ ዓመት የነበረውን የጥላቻ ግንብ በመናድ የሁለት ሀገር ነገር ግን አንድ ህዝብ ሆነን ለመቀጠል ትብብርና አብሮነታችን ወደፊት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሎ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በመግለጫው የትኩረት ማዕከል የነበረው ከእርቅ በኃላ መቀዛቀዝ ተፈጥሯል ተብሎ ለተነሳው ጥያቂ በአፅዕኖት ምላሽ ሰጠዋል፡፡

ይኸውም በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ምንም ዓይነት የግንኙነት መቀዛቀዝ የለም፡፡ የህወኣት የፕሮፓጋንዳ ሀይሎች ከመጀመሪያው ጀምሮ ደስተኛ ባለመሆናችው ህዝቡን ለማደናገር የሚለቁት የሀሰት ዜና ነው፡፡አያይዘውም በሁለቱ ህዝቦች መካከል የነበረው የአሮጋንትና የኃላቀርነተ የህወኣት የጥላቻ ግንብ በአዲሱ የለውጥ አመራር እንደምዕራብና ምስራቅ ጀርመን ግንብ ተንዷል፡፡

መንግስታዊ ግንኙነታችንም ከትብብር ባለፈ እንደ አንድ ሀገር መንግስት ነው የምንሰራው ፡፡ አብይም ሆነ ደመቀ መኮነን የኤርትራ ህዝብ መሪዎች ናችው፡፡እኔም ሆንኩ ሌሎች የኤርትራ አመራሮች የኢትዮጵያ ህዝብ አመራሮች ናችው፡፡ሁላችንም አንዳችን ለሌላችን አምባሳደሮች ነን፡፡በዚህ አጋጣሚ ግልፅ በመልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ጊዜያዊ ነው፡፡ ህወኣት ሃያ ሰባት ዓመት የቀበረው ፈንጅ ነው፡፡ ህወኣት ያደገበትን ሀገር የማተራመስ ተግባሩ የሚታወቅ ነው፡፡

እሰከ አሁን ባለን መረጃ በለውጥ አመራሮ ሆደሲፊነት እንጂ የህወኣት የጥፋት ቡድን ከአቅም በላይ አይደለም ፡፡ የኢትዮጵያን ህዝቦች አንድነት የሚፈታተን ችግር ለማስወገድ የኤርትራ ህዝብና መንግስት የኃላ ደጀን ነው፡፡ በዛሬው ዕለት አዲስ የሚገነባው የኤርትራ ኢምባሲ የመሰረት ድንጋይ በሁለቱ አመራሮች ተቀምጧል፡፡