በብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ላይ ዘለፋ መሰንዘራቸው የውሃ፣ መስኖና ኤሌከትሪክ ሚኒስትሩ ክደዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ክደዋል።

ኢትዮጵያ ተስማማችም አልተስማማችም የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ስጋት እውን ይሆናል። በአሜሪካና አለም ባንክ ጫና አብዛኛው ጉዳዮች ላይ ሀገራቱ መስማማታቸው ታውቋል።የሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በግብጽ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ እንደሚችል ፍንጮች ከሚኒስትሩ መግለጫ ታይተዋል።

የሕዳሴው ግድብ ድርድር ኢትዮጵያን እየጎዳ ነው ባሉ በብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ላይ ዘለፋ መሰንዘራቸው የውሃ፣ መስኖና ኤሌከትሪክ ሚኒስትሩ ክደዋል።አለም ባንክና አሜሪካ ኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዳደረጉባት ታውቋል።

የዓባይ ውሀ ተፈጥሯዊ ፍሰቱ በድርቅ ወይም በሌላ ምክን ያት ቢዛባ ግብፅ ማግኘት ይገባኛል የምትለውን የውሀ መጠን እንዳይነካ ሽፋን የሚሰጥ መመሪያ ይዘጋጃል የሚል ያስገቡት ነጥብ አሁን የኢትዮጵያን ተደራዳሪዎችና ባለሙያዎች እያወዛገበ ነው።የሕዳሴው ግድብ ድርድር እየተመራበት ያለው መንገድ የኢትዮጵያን ጥቅም እየጎዳ በመሆኑ ሊቆም ይገባል ተባለ:: የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ በጉዳዩ ላይ ከብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር መግባባት አቅቷቸው የቴክኒክ ቡድኑ አባላት ላይ ዘለፋ በመሰንዘራቸው ስብሰባው ረግጠው የወጡ ሙያተኞች መኖራቸው ተሰምቷል።

ውይይቱን የኢትዮጵያንም ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ ማስቀጠል ከተቻለ መልካም : ካልሆነ ግን የሶስትዮሽ ውይይቱን ኢትዮጵያ ያለምንም ተጨማሪ እርምጃ ማቆም አለባት ነው ያሉት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት። በቀጣዩ የፈረንጆቹ ጥር 8 እና 9 ቀን 2020 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ስብሰባ ከስምምነት ይደረስባቸዋል ተብሎ ይታመናል ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ፥ ካልተስማሙ የግድቡን ውሃ አሞላልና አስተዳደር የሚያካሄድበትን ህግ አንቀጽ 10 በስምምነት ይተገበራል ብለዋል። አንቀጽ 10 የሚተገበር ከሆነ የምንወስደውን አማራጭ መንግስትን አማክረን እንወስናለን ነው ያሉት ሚኒስትሩ። #MinilikSalsawi

የበለጠ መረጃ እነዚህን ሊንኮች ተጭነው ያንብቡ ፦
https://mereja.com/amharic/v2/185465
https://mereja.com/amharic/v2/187539