“ቤተ ክርስቲያን ሆይ፥ ፀሐይሽ አትጠልቅም” ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ታኅሣሥ 5 በሚሌኒየም አዳራሽ ይካሔዳል፤ ጸሎተ ምሕላ – ስብከተ ወንጌል – ቃለ ተዋስኦ – ድጋፍ ማሰባሰብ

ጸሎተ ምሕላ ጸሎት ይደረጋል፤ ወቅታዊ ፈተናዋ ይተነተናል፤ ድጋፍ ይሰበሰባል፤ 30ሺሕ የመግቢያ ትኬቶች በስርጭት ላይ ናቸው! ~~~ በአገልጋይ ዕጦት የተዘጉ፣ በፀራውያን ጥቃትና ተጽዕኖ የተዳከሙ ሦስት የኦሮሚያ አህጉረ ስብከት አብያተ ክርስቲያንን ለማስከፈትና ለማጠናከር፣ ገቢ የማሰባሰብ ዓላማ አለው፤ በሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ከ800 በላይ የገጠር አብያተ ክርስቲያን ናቸው፤ ከ3ቱ አህጉረ ስብከት ጠቅላላ …