በህብረብሄራዊነት በተጋመደ አንድነት ወደ ኢትዮጵያ ብልጽገና የተጀመረው ጎዞ መበየኛዎች

በኤ.የ.ሀ

የፌደራሊዝም ዋንኛ የትርጉም መገለጫ የመንግሰት ስልጣን የሚጋራበት እና የሚከፋፈልበት ሁለት መሰረታዊ ጽንሰ-ሀሳቦችን የሚያራምድ የፖለቲካ ስርኣት ነው፡፡ እነዚህ መርሆች እራስን-ማስተዳደር በራስ ጉዳዮች (self-rule) እና የጋራ አስተዳደር በጋራ ጉዳዮች (shared-rule) አቀናጅቶ በመያዝ የሚፈጠር ማንኛውንም የመንግስት አወቃቀርን የሚመለከት ሰርኣት ነው፡፡ ስልጣንን በማከፋፈልና በማጋራት የፌደራሊዝምን ፍልስፍና ተከትለው የሚፈጠሩ የተለያዩ የመንግስት አወቃቀሮች (ኮንፌደሬሽን፣ ያልተማከለ መንግስት፣ ) የሚኖሩ ሲሆን አንድ ሰርኣት ፌደሬሽን ነው የምንለው፣ በፌደራሊዝም ሁለቱ መሰራታዊ መርሆችን ማለትም አይነትነትን (ልዩ ልዩነትን ወይም አንድ አይነት አለመሆንን) እራስን-ማስተዳደር በሚለው መርህ የተዛመደ ተጋሪነትን በአንድነትን  የጋራ አስተዳደር በማጋመድ የራስና የወል አስተዳደደር ባነድነት የሚከትሙበት ሀገረ መንግሰት የሚደራጅበት በሀቀኝነት የሚሰራበትን ሰርአትና ተቋማዊ አደረጃጀትን የሚፈጥር  ነው፡፡ ስለሆነም ፌደራሊዝም አይነትነትን (diversity) በራስ የማስተዳደርን እና የተጋመዱና የተዛመዱ ትስስሮች (shared values and interests) በወል በአሀዳዊነት ወይም በአንድነት የሚተዳደሩበትን ሁኔታ)  አዛምዶ አቻችሎ አስማምቶ የሚያኖር ስረኣትና ዘዴ ነው፡፡ እራስን ማስተዳደደር እና በጋራ በአሀድ የማስተዳደር ጉዳዩች ሁለቱም አስፈላጊ አንዱ ካላንዱ የማያስፈልግ ያንዱ መኖር ሌላው መኖር አስፈላጊ የሆኑ የሁለት ሳንቲም አንድ ገጽታዎች ናቸው፡፡ አንዱ ላይ አተኩሮ ሌላውን መዘንጋት ያልተገባ ብቻ ሳይሆን ዋጋ ያስፈልጋል፡፡
 
የፌደራሊዝም መሰረታዊ ጥቅሞች
 
ሀገራት የፌደራል ስርኣት በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ መልካምድራዊ ገፊ ምክንያቶች ተግባራዊ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካ የፌደራል ስርኣት መፈጠር ዋና ገፊ ምክንያት ናቸው ተብሎው ከሚጠቀሱት ውስጥ የተሻለ ህብረት በመፍጠር ከወቅቱ የአሜሪካ ባላንጣና የቀድሞ ቀኝ ገዥ ታላቋ ብሪታንያ ሊቃጣ ከሚችል ወረራ እረስን ለመካላከል የሚስችል ህብረት ለመፍጠር እንደሆነ የሚጠቀስ ሲሆን፣ የላቲን አሜሪካ ሀገራት የሆኑት ብራዚልና አርጀነቲና ለአስተዳደር አመቺነት፤ በህንድ የተላያዩ የቋንቋ ቡድኖችን እራስን የማስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ፣ በናይጄርያ በትላልቅ የሀጋሪቱ ሶሰት ጎሳዎች/ብሄሮች መካከል የነበረውን ደም አፋሳሽ ግጭትና ይሄን ተከትሎ የተፈጠረውን የሀጋሪቱን ህልውና መናጋትና የሌሎች ህዳጣን ጎሳዎችን መደፍጠጥ ለማቆም ፌደራልዚም ተመራጭ ስርአት ሆኖዋል፡፡ እንግዲህ ፌደራሊዝም በአለም ላይ ምርጥና ወደር የማይገኝለት ስርአት ነው (እንዲህ ሊባል የሚችል ስርኣት በአለም ላይ አለ የሚባ ከሆነ) ማለት አይቻልም፡፡ እንዲያውም ከተለያዩ መንግስታት መኖር አንጻር ከኢኮኖሚና ከአስተዳደርና ውሳኔ አሰጣጥ ተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅ፣ በክልሎች መካከል ሊፈጠር ከሚችለው ያልተጋባ የፖሊሲና የተቋማት ውድድር፣ ከተፈርሮ ሀብትና መሰል ጉዳዮች ክፍፍልና ተጠቃሚነት አንጻር የፌደራሊዝም ስርአት በጥንቃቄ ተቀርጾ በብልሀት ተግባራዊ ካልሆን የግጭትና ክፍፍል ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡  ባጠቃላይ የፌደራል ስርአት ከሌሎች ስርአቶች ተመራጭ የሚደርጉት አንጻራዊ  ጥቅሞች የሚከተሉት እንደሆነ  ምሁራን ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህም
 
1. የመንገስት ስልጣን በመገደብ መንግስትን መግራት (combating concentration of power) ፡- ስልጣን በመአከል፣ በክልል እና/በአካባቢ መንግስታት መካከል በህገ-መንግስት  መከፋፈሉ ያልተገደበ ስልጣን እንዳይኖር በማድረግ የስልጣን በአንድ ቦታ መከማቸት የሚፈጥረውን የመንግስት አመባገንነትን ለመገራት የሚያስችል የስልጣን መቆጣጠርያና የተጠያቂነት ስርአትን ማስፋት

2. ተጨማሪ መንግስትን የመቆጣጠርያ ሰርአት ለዜጎች መፍጠሩ (multiple checking and accounting means against government power at different levels). የተለያዩ መንግስት መኖራቸው ዜጎች በአካባቢ፣ በክልል እና/ወይም በማእከል መንግስት ባሉ ተቋማትና አሰራርስርኣቶች (በምክር ቤቶች፣ በፍርድ ቤቶችና በሌሎች ተቋማት በመጠቀም)  መንግስትን የመጠየቅ፣ በውሳኔ የመሳተፍና ምንግስትን ተጠያቂ የማድረግ እድሉ የሰፋ ይሆናል፡፡
 
3. ግጭቶችን የመፍቻና የማስታረቅ  ( means of conflict resolution) ፡- የተደራጁና የተንቀሳቀሱ የማንነት ልዩነቶች ተቋማዊ በሆነ መንገድ የሚሰተናገዱበትን ያራስን እድል በራስ የመወሰን የቡድን ጥያቄዎችን የሚፈቱበትን ስርኣት በመዘርጋት ፌደራሊዝም በአዳይነት/ማእከላዊ ሀይሎችና በልዩነት/ልዩን ሀይሎች መካከል የሚነረውን የተቃርኖ ግንኞነቶችን በማስታረቅ አንድነትና ልዩነት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚሰተናገዱበትን ስርኣት በመዘርጋት በጠቅላይነትና በተገንጣይነት ሀይሎች መካከል ድልድይ በመስራት ግጭቶችን መፈታት፡፡ ይህንንም ሮናልድ ዋትስ የተባሉት ምሁር እንዲህ የገልጹታል ‹In the contemporary world, federalism as a political idea has become increasingly important as a way of peacefully reconciling unity and diversity within a political system.›
 
4. የተሻለ የፓሊሲ አማራጭ እንዲኖሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ (Policy innovation)  ክልሎች በራሳቸው እውቀትና ችሎታ እንዲንቀሳቀሱ እድል የሚሰጥና የክልል መንግሥታት የራሳቸውን ፖሊሲዎች ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንጣር  በማውጣትና በመተግበር የፖሊሲ አማራጮች እንዲኖሩ እድል የሚፈጥርና ለአካባቢያዊ ችግር አከባቢያዊ መፍትሄ (local solution for local problems) ለመስጠት ምቼ ስርኣት መሆኑ

6. መንግስትና ህዝብ ማቀራረቡ (bringing government closer to each other) የክልልና አከባቢያዊ መንግስታት መኖራቸው ዜጎች በአካባቢና በክልል መንግስታት ባሉ ተቋማትና አሰራርስርኣቶች (በምክር ቤቶች፣ በፍርድ ቤቶችና በሌሎች ተቋማት) የሚሳተፉበት ህገ-መንግስታዊ የዲሞክራሲ፣ የፍትህና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት እንዲዘረጉ ማድረጉ፤
 
7. የስልጣን መአከላት እንዲባዙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ (multiple centers of power flourishes) ክልሎችና የአካባቢ አስተዳደሮችና ከተሞች የራሳቸውን ፖለቲካዊ፣ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማእከሎችን እንዲገነቡና የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ በማእከላዊ መንግስት ከተማ ብቻ እንዳይከማቹ በማድረግ የሀብት፣ የባህልና የፖለቲካ ማእከላት በተለያዩ ቦታዎች እንዲያብቡ በማድረግ የሀብትና ስልጣን ፍትሀዋ ስርጭት እንዲኖር የሚየስችል መሆኑ
 
8. የዜጎችን አማራጮች መስፋቱ (expanding citizens choices)፡- በፌደሬሽ አባላት መካከል በሚደረገው ጤናማ ውድድር በሚፈጠረው መልካም እድሎች ዜጎች የተሸለ ጥቅም (ዊልፌር፣ የስራ እድል፣ ደሞዝ ወዘተ) ወደሚያገኙበት መሄድ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር የሚችል መሆኑ፤
 
በህወሀት መሪነት ላለፉት 26 አመታት የተተገበረው የፌደራል ስርአት ከላይ ከተዘረዘሩትየታወቁ መስፈርቶች አንጻር ምን ይመስል ነበር?  የብልጽግና ፓርቲስ ከነዚህ መስፈረቶች አንጻር ሲበየን የድርጅቱ አወቃቀር ሆነ ፕሮግራም ምን ይመስላል?
 
የብልጽግና ፓርቲ ጅምሮች — ከይስሙላ ወደ ሀቀኛ የፌደራል ስርአት?
 
በህወሀት መሪነት ላለፉት 26 አመታት የተተገበረው የፌደራል ስርአት ከላይ ከተዘረዘሩት የታወቁ መስፈርቶች አንጻር ምን ይመስል ነበር? የብልጽግና ፓርቲስ ከነዚህ መስፈረቶች አንጻር ሲበየን የድርጅቱ አወቃቀር ሆነ ፕሮግራም ምን ይመስላል? በመሰረቱ የአንድ ፓረቲ ድርጅት አወቃቀር ምንም ቢመስል ዋና ጉዳዩ ከላይ የቀመጡትን መመዘኛች እንዴት በተግባር ያሳክል የሚል ነቅ ዋና ቁም ነገሩ፡፡
 
በህውሀት መሪነት ላለፉት 27 አመታት የተተገበረው የፌደራል ስርአት ልዩነትን ከውበት መገለጫ ባሻገር በሀቀኛ እራስን የማስተዳደደርና በገራ ጉዳዮች ትርጉም ባለው መልኩ ሁሉም የሁሉም ክልሎች/ብሄሮች ተሳትፎ የጋራ አስተዳደር ተግባራዊ አላደረገም፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ  ከህገ መንግስቱም በላይ ቦታ ተሰጥቶት ሁሉንም ነገር የሚወሰነው በመአከል ነበር፡፡ የክልል መንግሥታት የራሳቸውን ፖሊሲዎች በማውጣትና በመተግበር ሀቀኛ ፌደራል ስርአት አልተየም፡፡ ብሄሮች ከምግብ ከልብስ ከጭፈራ ሌላ በላፉት 27 አመት የተረፋቸው ነገር አምብዛም ነው፡፡ ሕገመንግስት፤ ፌደራሊዝም በዴሞክራሲ መግራት ማጠናከር አልተቻለም፡፡ የተለያዩ ቡድኖችን የፖለቲካ አመለካከቶችና  የተለያዩ ኃይሎች፣ ብሄሮች ዋናና አጋር ሳይባሉ በመአከላዊ መንግሰት የሚሰተፉበት የሚወስኑበት የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር አልተቻለም የህግ የበላይነት ነጻ ምርጫ ፍትህ የመደራጀትና የሚዲያ ነጻነት በህወሀት/ኢሀዴግ መልካም ፍቃድ የሚለገሱ ቅንጦቶች ነበሩ፡፡ የኢኮኖሚ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር፣ የዲፕሎማሲ፣ የወታደራዊና የሕዝብ ደኅንነት ሥልጣን በአንድ ጎሳ ብቻ ተይዞ ሲዘወር ቆይቷል፡፡ የልማት ፖሊሲና ፕሮጀክቶች በመአከል ተጠርንፈው ክልሎች ይሄነው የሚባል ሚና ያልነበራቸው ሲሆን የህወሀት ሹማምነትና ጀነራሎች መጨወቻና መለማመጃ የነበሩ ስለመሆኑ የሜቴክ የስኳር ፕሮጀከቶች የማዳበርያ ወዘተ ያደረሱት ኪሳራ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ባጠቃላይ ህውሀት በትግባር አህዳዊ ስርአት ብቻ ሳይሆን አስፈኖ የነበረው ጭልጥ ያለ አምባገነናዎ አህዳዊ የአፓርታይድ ስርአት ነበር፡፡ በመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም ሆነ አደረጃጀት ሊበየን የሚገባው የህውሃትን የአፓርታይድ ስርአት አስቀጥሏል ወይስ አራግፎ ጥሎ ሀቀኛ ህብረ-በሄራዊ በእኩልነት በህዝቦች የጋራ መልማትና የመጠቀም መብትን መሰረት ያደረገበተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ ፍትሀዊና ዲሞክርራስያዊ ስርአት  አንድነትን እውን ለማደረግ ከሚታሰቡና ከሚፈጸሙ ጉዳዮች ጋር መሆን አለበት፡፡
 
ሀቀኛ የፌደራል ስርአት ውስጥ አንድነት ዋንኛው ጉዳይና የህብረ-ብሄራዊነት ካስማ ስለመሆኑ

በመሰረቱ በአንድ ሀገር ውስጥ ህዝቦችን የሚያሰተሳስሩ ጉዳዩች የጋራ ታሪኮች የዛሬና የነገ የማይነጣጠሉ የወል እጣፋነታዎች ከሌሉና የማይኖሩ ከሆነ የፌደራል ስርአት አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ምንጫችን ብልጽገናችን ሆነ ውድቀት እጣፋንታችን የማይነጣጠል የተሰናሰለ አብሮ መኖራችን ለጋራሆነ ለተናጥል ጠቅሞቻችን ማበብ በሰላም ለመኖር ለማደግ በአለም መደረክ የተሻለ ሀይልና ተሰሚነትን ለማግኘት አብሮ መኖር አስፈላጊ ካልሆነ በፌደሬሽን በአነድ ሀገር ውስጥ መኖር አስፈላጊነቱ እምበዛም አይደለም ከወጪ በስተቀር፡፡ ለዚህም ነው በፌደራል ስረአት ውስጥ በተለይም በህበረ-በሄራዊ ፌዴሬሽኖች ውስጥ እራስን ማስተዳደደር እና በጋራ በአሀድ የማስተዳደር ጉዳዩች ሁለቱም አስፈላጊ አንዱ ካላንዱ የማያስፈልግ ያንዱ መኖር ሌላው መኖር አስፈላጊ የሆኑ የሁለት ሳንቲም አንድ ገጽታዎች መሆናቸው፡፡ አንዱ ላይ አትኩሮ ሊላውን መዘንጋት ያልተገባ ብቻ ሳይሆን  የሚስከፍለው ዋጋ በሀገራችን ላለፉት 27 አመታት እንዳየነው አክሳሪ ነው፡፡
 
በህብረ-ብሄራዎነት የተደመረ አንድነት ሊትዮጵያ ብልጽግና/ Multinational Synergized Unity to Ethiopia’s Prosperity
 
የሰሞኑ ብልጽግና ፓርቲ ምስረታ ጉዳይ መታየት መተንተንና መበየን ያለበት ካለፉት 26 አመታት የታዩትን ችግሮች እንዴት ይፈታል የብሄሮችን በራሳቸው ጉዳይ የመወሰን መብታቸውን በጋራ የሀገራዊ ጉዳዩች ዋና ባለቤትና አጋር ሳይባሉ የዳሩም ሆነ የመሀል ሀገር ሁሉም ብሄሮች ድምፃቸው የሚሰማበት እድል የመፈጠር የመደራጀት መብትን ሀሳብን የመገለጽ ነጻነትን እንዴት በፖሊሲ በተግባር ያከብራል ያሰከበራል ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ሰዋዊ ልማቶችን እንዴት አውን ያደረግል በሚሉ የመፋረጃ መስፈርቶች መመስረት አለበት፡፡ ባጠቃላይ ሀቀኛ የፌደራል ስርአትን አውን ከማደረግና ካለማደረግ ጉዳዮችጋር መሆን ይኖርበታል፡፡ እውነተኛ ፌደራሊዝም ካለዲሞክራሲ እኩልነት እና የጋራ የሀገር ባላቤትነት በተግባር ከመፈጸም አንጻር የሚመዘን ሲሆን የብልጽግና ፓርቲ ከነዚህ መስፈረቶች አንጻር የወሰዳቸው ተራማጅ እርምጃዎች ለምሳሌ ዋና ብሄሮችና ደጋፊ ብሄሮች የሚለውን ክፍፍል ማስቀረቱ የዜግነት መብት በህገመንግስቱ ሰፍኖ ሳለ ለረጅም ግዜ በተግባር መዘንጋቱ ያደረሰውን ቀውስ ለማስተካከል እየተሰራ ያለው ስራ የመደራጀትና ሀሳብን የመገለጽ መብትን ለማክበር የብሄሮችን የራሳቸውን ከልል የመመስረት መብት ለማሰከበር በሲዳማ ጉዳይ በተግባር ያሳየው ስራ ወዘተ የፓርቲውን ተራማጅነት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን ሀቀኛ የፌደራል ሀይል መሆኑንም ጭምር ነው፡፡ በመጨረሻም ለጸረ-ፌደራሊስቷ ህወሀት የሚከተለውን ዜማ በመጋበዝ ጽሁፌን ላብቃ፤
 
ወደ ኋላ ሄደሽ በሀሳብ ከማለም
ቀን እንዳይመሽብሽ ትናነት ዛሬ አይደልም፡፡