ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በኖቤል ሽልማት ወቅት ለጋዜጠኞች መግለጫ እንደማይሰጡ ተሰማ

“ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር”— የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር

Elias Meseret — “የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት”— የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም

የኖርዌይ የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦላቭ ጆልስታድ ጠ/ሚር አብይ ከአምስት ቀን በሁዋላ ሽልማታቸውን በሚቀበሉበት ወቅት ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ፕሮግራም ላይ እንደማይገኙ ገልፀው “ይህ በጣም ችግር ነው። ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር” ብለው ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል።

ዛሬ የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም በላከችልኝ መረጃ “የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት። ስለዚህ ጠ/ሚሩ በተመረጡ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ላይ ከኖቤል ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር ይካፈላሉ” ብላለች።

በነገራችን ላይ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በ2009 የኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት የሚድያ ፕሮግራሙ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተው ነበር።