የኢዜማ አመራር ስለብልፅግና ፓርቲ እና ኢዜማ የውሕደት ንግግር ማስተባበያ ሰጡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢዜማ አመራር ስለብልፅግና ፓርቲ እና ኢዜማ የውሕደት ንግግር ማስተባበያ ሰጡ

– ብልፅግና ፓርቲ እና ኢዜማ ለመዋሃድ ንግግር ጀመሩ… go.shr.lc/2sCcJB2

– ብልፅግና ፓርቲ ከኢዜማ ጋር ሊዋሀድ ነዉ የሚለዉ ሀሰት መረጃ ነዉ – የኢዜማ ወጣት አደረጃጀት ሀላፊ ፅዩን ግርማ

አንዳፍታ – ዛሬ ረፋዱን የብልፀረግና ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ሊዋሀዱ ነዉ ተብሎ ሲሰራጭ የነበረ ዜና ተመልከተናል፡፡

ሁለቱ ፓርዎች በተነፃፃሪ የሚያንፀባርቁትን ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ሊዋሀዱ እንደሚችሉ ከወዲሁ ትንበያቸዉን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

ይህንን ተከትሎ መረጃ ተሌቪዥን የሚባል የዩቱብ ሚዲያ ቻናል አዲስ የተመሰረተዉና ምናልባትም ለ2012 ምርጫ በዶክተር አቢይ አህመድ እየተመራ እንደሚቀርብ የሚጠበቀዉ ብልፅግና ፓርቲ ከወራት በፊት በፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፣ የሽዋስ አሰፋና ሌሎችም እዉቅ የፖለቲካ ሰዎች የመሰረቱት ኢዜማ ጋር ሊዋሀድ ንግግር ጀምሯል የሚል መረጃ አሰራጭቷል፡፡

ዘገባዉ እንደሚለዉ ኢዜማ ከብልፅግና ፓርቲ እንዲዋሀድ ጥሪ ያቀረቡት የብልፅግና ፓርቲ አደራጅ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ናቸዉ፡፡

የኢሀዴግን ሶስት ግንባር ፓርቲዎች ያዋሀደዉ ብልፅግና ፓርቲ ጥሪ ያቀረበዉ ሊኢዜማ ብቻ እንዳልሆነ እና ሌሎች የፖለቲካ ሀይሎችም ግብዣ እንደቀረበላቸዉ መረጃ ቲቪ ያትታል፡፡

አንዳፍታ ይህንን ዜና ለማጣራት ወደ ኢዜማ የስራ ሀላፊዎች ደዉሎ መረጃ አግኝቷል፡፡ የኢዜማ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ናትናኤል አበራ ስልክ አይመልሱም – በሳቸዉ ምትክ ለጥያቄያችን ምላሽ የሰጡን የወጣት አደረጃጀት ሀላፊ ፅዩን ግርማ ይህ መረጃ ፍፁም ሀሰት ነዉ ብላለች፡፡

እንደ ፅዩን ገለፃ እስካሁን ድረስ ኢዜማዎች ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ተቀላቀሉ የሚል አንዳችም ይፋዊ ደብዳቤ አልተላከልንም – ሊዋሀዱ ነዉ ተብሎ የወጣ መረጃ ካለም ስህተት ነዉ፡፡

መረጃዉ በዚህ ስአት የኢዜማ እና ብልፅግና ፓርቲ መሪዎች ለመዋሀድ ዉይይት እያደረጉ ነዉ ይላል፡፡ ስለሆነም ለፅዩን ያቀረብንላት ጥያቄ ምና አልባት በዚህ ስአት የፓርቲዎቹ መሪዎች ለናንተ መረጃዉ ሳይደርስ እየተወያዩ ቢሆንስ የሚል ነዉ፡፡

የፅዩን መልስ ግን በዚህ ስአት የምገኝዉ ከፓርቲዉ መሪዎች ጋር ነዉ የሚል ነዉ፡፡