በሶማሌ ክልል አቶ ሙስጠፌ የሚመራው ሶዴፓ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፀደቀ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) ዛሬ ባካሄደው ጉባዔ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቆታል።

ፓርቲው ድርጅታዊ ጉባዔውን ዛሬ አካሂዷል።

በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔ የሶዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ማእከላዊ ኮሚቴ ቀደም ብሎ የብልጽግና ፓርቲን ለመዋሃድ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ከመከረ በኋላ ነው የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) አባል እና አጋር ድርጅት የሆኑ ፓርቲዎች ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል በጉባዔያቸው ውሳኔ ያሳለፉ ድርጅቶች ቁጥር ስምንት መድረሱ ታውቋል።