አሳዛኝ ዜና!! የእውቁ ወልቃይቴ ቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ ተገደለ

ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. (June 1, 2018)

ለውጥ በየት በኩል እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም?! ዐማራ አሁን ባለችውና የቲፎዞ ፖለቲካው እንድትቀጥል በሚፈልጋት ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ የለውም። እቅጩን ስንነጋገር ይህን ይመስላል። አሳዛኝ ዜና!! የእውቁ ወልቃይቴ ቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ በትግሬዎች ተገደለ፡፡ ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. (June 1, 2018) ሳንጃሙሴ ባንብ ላይ አቶ ግዛቸው አዳነ በወያኔ ቅጥረኞችና በትግራይ ልዮ ሀይል አባላት በተከፈተበት ተኩስ በ9 ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል፡፡

የጀግናው የወልቃይት አስተዳዳሪ የቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጂ በወልቃይት ጉዳይ እየተንቀሳቀሰ ይገኝ ነበር፡፡ ታላላቅ ሰዎችን በመግደል የወልቃይት ጉዳይን እናዳፍናለን ብለው ከላይ ታች እየባዘኑ ነው፡፡ ግዛቸው ወደ ጎንደር እያመራ ነበር፡፡ ነብስህን ይማር!! አንድ በአንድ ከማለቃችን በፊት በዐማራዊ አንድነት እንቁም!

ማስታወሻ፤ ዘወትር የሞት ዜና አታብስሩን ለምትሉን ገዳዮቻችን ገድለን ሞትን ድል እስክናደርግ ድረስ እውነቱን መዘገባችን አናቆምም!

(ከፌስቡክ የተገኘ)