የአማራና ኦሮሞ ምሁራን መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

Image may contain: 6 people, people sitting, table and indoor

የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ እና ለመንግሥት የመፍትሔ ምክረ ሐሳብ ለማቅረብ ያለመ የአማራና ኦሮሞ ምሁራን መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የኦሮሞ እና አማራ የምሁራን መድረክ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የህዝቦችን ትስስርና የሃገርን አንድነት ለማጠናከር ይመከራል።

ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱ ክልል ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ተመሳሳይ የህዝብ ለህዝብና የምሁራን መድረኮች ከዚህ ቀደም መካሄዳቸው ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም በቅርቡ የሁለቱ ክልል ባለሃብቶች እና የወጣቶች የውይይት መድረክ መካሄዱም የሚታወስ ነው።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ታየ ደንድአ ‹‹ከተወያየንና ሐሳብ ከተለዋወጥን የማንፈታው ችግር የለም›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአማራና ኦሮሞ አንድነት ለራሳቸው ሕዝቦች ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ለኢትዮጰያ አንድነት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ በዋናነት የኢትዮጵያን አንድነት የማይፈልጉ አካላት አማራና ኦሮሞን ማጋጨት እንደሚፈልጉ ግልጽ መሆኑን በማመላከት ‹‹ይህ ከእናንተ ከምሁራን የተደበቀ አይደለም›› ብለዋል

‹‹ሕዝብ በተሰበሰበበት አካባቢ ሁሉ የሚነሱ አለመግባባቶችን ሁሉ ሥረ መሠረታቸውን ፈልጎ ማግኘት አስፈላጊ ነው›› ሲሉም አቶ ታዬ አሳስበዋል፡፡

በዚህ የምክክር መድረክ የሕዝቦችን የጋራ እሴት እና አንድነት የሚጠቅሱ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

AMMA


► መረጃ ፎረም - JOIN US