ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች በምዝገባ አዋጁ ዙሪያ አለመስማማታቸው እንቅፋት እንደሆነበት አስታወቀ፡፡


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ቀጣዩን ምርጫ ለማስኬድ እየተዘጋጀ ቢሆንም ፓርቲዎች በአዋጁ ዙሪያ አለመስማማታቸው እንቅፋት እንደሆነበት ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ዙሪያ የጠራው ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁን በተመለከተ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ፓርቲዎቹ ሐሳብ ሰጥተውበት በፓርላማ የጸደቀ አዋጅ ቢሆንም ለተፈጻሚነቱ ወደፊት ከመምጣት ይልቅ በየጊዜው አዲስ ሐሳብ በማንሳታቸው መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡

አዋጁን ተከትሎ የወጡ 39 መመሪያዎችን በተመለከተ ከፓርቲዎቹ ጋር ውይይት ቢደረግም አሁንም የጊዜ ገደብ በሌለው መልኩ ፓርቲዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ማንሳታቸውን አመልክተዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከፓርላማው ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉም የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ጠቁመዋል፡፡ የ2012ን ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ ቦርዱ በጥሩ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Source – AMMA