የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬ ውሎው በሚዋሐደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጎ መፅደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው እንደገለፁት ኮሚቴው ከትላንቱ የፓርቲ ውሕደት ወሳኝ ውይይት በመቀጠል ዛሬም በሚዋሐደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ተመካክሮ ማጽደቁን አብስረዋል።
ትላንት ካደረግነው የፓርቲ ውሕደት ወሳኝ ውይይት በመቀጠል ዛሬም በሚዋሐደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ተመካክረናል:: በፓርቲ ፕሮግራሙ ላይ ተወያይተን ማጽደቃችንን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው::
— Abiy Ahmed Ali (@AbiyAhmedAli) November 17, 2019
አዲሱ ፓርቲ የኢትዮጵያን የፌደራል ሥርዓት እና ዴሞክራሲን ያጠናክራል፤ አካታች ሆኖ ብዝኃነታችንን ያከብራል፤ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኅብረ ብሔራዊነትን ያከበረ አንድነትን መሠረት እንደሚያደርግም ገልፀዋል።
*******************************************************************
የኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ የመተዳደሪያ ደንብን ከታች ያለውን ሊንክ/ምስል በመጫን ማውረድ (Download) ይቻላል።
ምንጭ፦ Addis Standard