የሕወሓት አመራሮች ወደ መቐለ መመለሳቸው ተረጋግጧል።

የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አመራሮች መካከል የተወሰኑት ወደ መቐለ መመለሳቸውን ዶይቼ ቬለ አረጋግጧል። ኢሕአዴግ በስብሰባ ምን ያክል የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ እንደተሳተፉ ያለው ነገር የለም።

DW : ኢሕአዴግ ሲዋሐድ የሚመራበት ፕሮግራም ለግንባሩ ምክር ቤት እንዲቀርብ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መስማማቱን አስታወቀ። የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ በሁለተኛ ቀን ውሎው ውህድ ፓርቲው በሚኖሩት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የውጭ ጉዳይ መርሐ-ግብሮች ላይ ውይይት አድርጓል።

ኢሕአዴግ ሲዋሐድ «አካታች የሆነ የካፒታሊዝም ሥርዓት» ለመፍጠር ያቀደ የኤኮኖሚ ፕሮግራም እንደሚከተል አስታወቀ። ለሁለተኛ ቀን ውይይት ሲያደርግ የዋለው የኢሕአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ በሁለተኛ ቀን ውሎው ውህድ ፓርቲው በሚኖሩት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የውጭ ጉዳይ ፕሮግራሞች ላይ ውይይት አድርጓል።

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ትናንት የኢሕአዴግን ውህደት በስድስት ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምፅ ሲያጸድቅ ከተሳተፉ የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አመራሮች መካከል የተወሰኑት ወደ መቐለ መመለሳቸውን ዶይቼ ቬለ አረጋግጧል። ኢሕአዴግ በዛሬው ስብሰባ ምን ያክል የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ እንደተሳተፉ ያለው ነገር የለም።

አቶ ፍቃዱ በቅርቡ ይጠራል ላሉት የኢሕአዴግ ምክር ቤት በሚቀርበው አዲስ ፕሮግራም በኤኮኖሚው ረገድ «አካታች የሆነ የካፒታሊዝም ሥርዓት ለመፍጠር» ያቀደ መርኅ እንደሚከተል ተናግረዋል።

«እንደ ሌሎች አገሮች ጥቂቶች ብቻ ሐብታም የሚሆኑበት አብዛኛው ደሐ የሚሆንበት ሳይሆን፤  አብዛኛው ፍትኃዊ የሆነ የሐብት ክፍፍል እንዲኖረው ለማድረግ እና ሁሉም በየደረጃው የሚጠቀምበት ካፒታሊዝም ሥርዓት» በመፍጠር ላይ ትኩረት አድርገው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ መወያየታቸውን አቶ ፍቃዱ ለብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ገልጸዋል።

Äthiopien | Abstimmung EPRDF (EPRDF) በሁለተኛው ቀን ስብሰባ የተወሰኑ የሕወሓት አመራሮች አልተገኙም

የአገሪቱ ኤኮኖሚ ከግብርና ጥገኝነት በማላቀቅ ሌሎች የምጣኔ ሐብቱ ዘርፎችን ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮግራም ፓርቲው እንደሚከተልም ተናግረዋል። «ባለፉት ጊዜያት የነበሩ ሕፀጾችን በማረም ትክክለኛ የነፃ ገበያ ሥርዓት» በመገንባት ላይ የፓርቲው ፕሮግራም ትኩረት እንደሚያደርግ የገለጹት አቶ ፍቃዱ «የመንግሥት ጣልቃ ገብነት በተመረጠ አግባብ፤ የመንግሥትን የሥርዓት ጉድለት እና የገበያ ጉድለትን የሚያርም በሒደት የግል ባለሐብቱን እያሰፋ የሚሔድበት ዕድል እንዲኖረው ለማድረግ የተቀመጠ ነው» ብለዋል።

ኢሕአዴግ ባለፉት አመታት ይመራበት የነበረው የልማታዊ መንግሥት ሞዴል እጣ ፈንታ በሥራ አስፈፃሚው ውይይት ተነስቶ እንደሆነ አቶ ፍቃዱ ያሉት ነገር የለም።

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር «ትላንት ካደረግነው የፓርቲ ውሕደት ወሳኝ ውይይት በመቀጠል ዛሬም በሚዋሐደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ተመካክረናል። በፓርቲ ፕሮግራሙ ላይ ተወያይተን ማጽደቃችንን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው።» ብለዋል።

በፖለቲካ ረገድ «ጠንካራ ኅብረ-ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ እና ፌደራላዊ ሥርዓት መፍጠር፤ የብሔር እና አገራዊ ማንነቶችን እንዴት ማስታረቅ ይቻላል?» የሚሉ ጉዳዮች በፕሮግራም እና በሕገ-ደንብ መካተት አለባቸው ከተባሉ መካከል እንደሚገኙበት አቶ ፍቃዱ አብራርተዋል።

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ የግንባሩን ውህደት አጸደቀ

አቶ ፍቃዱ ውሕዱ ፓርቲ «ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚያካትት፤ ፍትኃዊ ውክልና የሚረጋገጥበት መሆኑ በፖለቲካ ፕሮግራሙ ማኒፌስቶ መቀመጥ ስላለበት ይኸም ጎላ ብሎ ውይይት የተደረገበት ነው» ብለዋል።

የዴሞክራሲ ተቋማትን ገለልተኝነት የማረጋገጥ እና የማጠናከር፤ የጸጥታ፣ የደህንነት፣ የፖሊስ እና የመከላከያ ተቋማት ከፓርቲ ሥራ የመለየት፤ የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓት ግንባታን ማጠናከርን አስፈላጊነት በፕሮግራሙ ማካተቱን ጠቁመዋል።  አቶ ፍቃዱ እንዳሉት ኢሕአዴግ ሲዋሐድ በርከት ያሉ ቋንቋዎችን የሚጠቀም «ልሳነ-ብዝሃ» ይሆናል።

Äthiopien | Abstimmung EPRDF ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ቅዳሜ ማምሻ በስድስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ በውኅደቱ ላይ ከስምምነት ላይ ደርሷል።

በአቶ ፍቃዱ ማብራሪያ መሰረት ኢሕአዴግ ሲዋሀድ ለጤና አገልግሎት እና ለትምህርት ጥራት ትኩረት የሚሰጥ የማኅበራዊ ጉዳይ ፕሮግራም ይከተላል። የግብረ-ገብ ትምህርቶች እንዲሰጡም ይደረጋል።

በውሕድ ፓርቲው ፕሮግራም ላይ ዝርዝር ውይይት እና ክርክሮች መደረጉን የተናገሩት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ «በቅርብ ጊዜ ለሚጠራው ለኢሕአዴግ ምክር ቤት ረቂቁ እንዲቀርብ» መወሰኑን ለብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ማብራሪያ አረጋግጠዋል።

በሥራ አስፈፃሚ አባላቱ መካከል የተደረገው ክርክር «ምን እንጨምር? ምን እንቀንስ? እንዴት እናጎልብተው? እንዴት እናዳብረው?» የሚል እንጂ «መሠረታዊ ልዩነት» አለመኖሩን ገልጸዋል።

ብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ አቶ መለስ ዜናዊ፤ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር አቶ ስዩም መስፍን በውሕደቱ አስፈላጊነት ላይ በተለያዩ የኢሕአዴግ ስብሰባዎች የሰጧቸውን አስተያየቶች በመደጋገም አሳይቷል። ነገ በሕገ-ደንብ ላይ ውይይት እንደሚያደርግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ ተናግረዋል።