ኢሕአዴግ ሲዋሐድ «አካታች የካፒታሊዝም ሥርዓት» ለመፍጠር ማቀዱን አስታወቀ

ኢሕአዴግ ሲዋሐድ የሚመራበት ፕሮግራም ለግንባሩ ምክር ቤት እንዲቀርብ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መስማማቱን አስታወቀ። የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ በሁለተኛ ቀን ውሎው ውህድ ፓርቲው በሚኖሩት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የውጭ ጉዳይ መርሐ-ግብሮች ላይ ውይይት አድርጓል። …