“መንግስት ያስፈረመው የውል ወረቀት ጥቅሙ አልታያቹ ብሎናል” – የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግቢው በር በመዘጋቱ ሳቢያ በጥር እየዘለሉ ለመውጣት መገደዳቸውን እየገለፁልን ነው። መንግስት ምን እንድንሆን ድረስ እንደሚጠብቅ ግራ ገብቶናል ያሉት ተማሪዎች የጠበቃ ኃይሎች ግቢው ውስጥ ቢኖሩም ችግሮች ዶርም ውስጥ ድረስ የሚፈጠሩ በመሆኑ ተማሪውን ስጋት ላይ ጥሏል ሲሉ ገልፀዋል።
መንግስት ወረዳ ድረስ አንከራቶ ያስፈረምን ውል ጥቅሙ አልታያቹ ብሎናል፤ ችግሩ በቀላሉ የሚያይ አይደለም፤ ከኃላፊነት ጉድለት ወንድም ከወንድሙ፣ እህትም ከእህቷ እየተቃቃሩ ነው፤ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አሳበዋል።
ግቢ ውስጥ እንደልባቸው የሚፈነጩ ፤ ግቢ የሚያተራሙሱ ሰዎችን መቆጣጠር አለመቻችሉ የሚያሳዝን ነው በዚህ ሁኔታ ትምህርት መቀጠል ስለሚያስቸግር መንግስት ተማሪዎችን በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው ይሸኝ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል… በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አለመረጋጋት መፈጠሩን ተማሪዎች ገልፀውልናል። ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ ሳይደርሱ መንግስት ሊቁጣጠር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፤ በግቢው ውስጥ ባለው ስጋት ሳቢያም በርከት ያሉ ተማሪዎች ከግቢው መውጣታቸውን ጠቁመዋል።
Source : TIKVAH-ETH