ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ጉዳት ደርሶበት ህይወቱ አልፏል

ዩኒቨርስቲዎቻችን እንዴት አደሩ

ሰሞኑን የተለያዩ በዩኒቨርስቲዎቻችን ተከስተው የነበሩ የሰላም መደፍረሶችን ተከትሎ የተለያዩ ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ በዛሬው እለትም በነዚሁ ዩኒቨርስቲዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሚደረጉ ውይይቶች ቀጥለዋል፡፡ ውይይቶችን ተከትለው ያሉ ለውጦችንና አዳዲስ ክስተቶችን ሁሉም አካላት የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው ከዚህ በታች ተጠቃልሎ ቀርቧል፡፡

1. ውይይቶችን ተከትሎ በጅማ፣ በመቱ፣ በመደወላቡ፣ ወልደያ እና ወሎ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል፡፡ በዛሬው እለትም ቀሪ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

2. በተቀሩት ዩኒቨርስቲዎቻችን የመማር ማስተማር ሂደቱ በሙሉ ወይም በከፊል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

3. በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ በመታጠቢያ ቤት ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ያለ ሲሆን የጉዳቱ መንስኤ እና ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣሩ ይገኛሉ፡፡

4. አንድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪ ትናንት ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ከዩኒቨርስቲው ውጪ ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ ባሶ ትምህርት ቤት በሚባለው አከባቢ ጉዳት ደርሶበት ደብረ ብርሐን ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ቢደረግለትም ህይወቱ አልፏል፡፡ ፈጣሪ ነፍሱን ያሳርፍ፤ ለሟች ቤተሰቦችም መፅናናትን ይስጥልን! ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለሟቹ ዝርዝር መረጃ እና ስለአደጋው መንስኤ የተሟላ መረጃ ከደብረብርሃን ከተማ ፖሊስ እንዳገኘን የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ዩኒቨርስቲዎቻችን ሰላም እንዲሆኑ ሁላችንም ዜጎች ኃላፊነት አለብን! ስለሆነም ለዩኒቨርስቲዎቻችን ሰላም ኃላፊነታችንን እንወጣ!

ህዳር 5 ቀን 2012 ዓ.ም

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

http://moshe.gov.et/viewNews/91