ወላጆች ፈርመውበታል በዩንቨርስቲዎች አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በቂ ነው የተባለለት የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማትና የተማሪዎች ውል ምን ዋጠው???

አፈጻጸም ላይ ሿ ሿ !!
ተገኖ የተወራለት የሳይንስና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስቴር የተማሪዎችና የወላጆች ፊርማ የሰፈረበት ውል የት ገባ ???
 
ወላጆች ፈርመውበታል በዩንቨርስቲዎች አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በቂ ነው የተባለለት የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማትና የተማሪዎች ውል ምን ዋጠው??? የተዘጋጀው ለፕሮፓጋንዳ ነው ወይንስ ተማሪውን ለማስፈራራት ብቻ ??? በቂ አጥኚና መፍትሔ የሚያስቀምጡ ኤክስፐርቶች የሌሉት መንግስት የሕዝብን ሃብት ከማባከን ውጪ አንድም የረባ ስራ መስራት አልቻለም። ፊርማው ሳይደርቅ ዩንቨርስቲዎች አኬልዳማ ሆነዋል።
 
መጀመሪያ የአስተሳሰብ ልህቀት ላይ አልተሰራም። በመቀጠል ተማሪዎችን ወዳልተፈለገ ነገር የሚመሩ ነገሮች በመለየት የማስተካከያ እርምጃ  አልተወሰደም። የመንግስት በጀት በሰላም ኮንፈረንስና በስብሰባ ባክኗል።ተጠያቂነትንና ሐላፊነትን በሕግ የበላይነት አጣምሮ ያላሰፈነ መንግስት ከኪሳራ ውጪ ምንም አይፈይድም።
 
ተማሪዎችን በጥሩ ስነ ምግባር አንፀው ያላሳደጉ የሁለተኛ ደረጃ መምሕራንም ለዚህ ግጭት የራሳቸው ድርሻና ተጠያቂነት አለባቸው። ወላጆችም ልጆቻቸውን የመሩበት የ አስተዳደግ ዘይቤ ራሱን የቻለ ተፅእኖ ፈጥሯል። መንግስት በተለይ በፖለቲካው መስክ የሚከተለው አሻጥርና ሕገወጥ የፖለቲካ አካሔድ ከባድ አደጋን ከፊታችን ደቅኗል። በነዚህና በመንግስት ስንፍና ሕጎችና ደንቦች መመሪያዎች በተግባር ሊተረጎሙ ባለመቻላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤሩም ያዘጋጀው ውል ሿ ሿ ተሰርቷል። #MinilikSalsawi