በዶዶላ ጥቃት ፖሊስና የቀበሌ አመራሮች ተሳታፊ ነበሩ ሲሉ የጥቃቱ ሰለባዎች ተናገሩ

በዶዶላና አካባቢው ለደረሰው ጥቃት የአካባቢው ፖሊስና የቀበሌ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ በተፈፀመባቸው ጥቃት የተፈናቀሉ ወገኖች ጠየቁ።

ጥቃቱ በተፈፀምበት ወቅት ምንም አይነት ህግን የማስከር ስራ አለመስራታቸውን የገለፁት ተፈናቃይ ወገኖች ይባስ ብሎም የጥቃቱ ተባባሪዎች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ አሁንም በዶዶላ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንና በሌሎችም አካባቢዎች በርካታ የጥቃቱ ሰለባ ዜጎች ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን በጥቃት አድራሽ ቡድኖች የተፈጸመባቸውን ግፍ ተናግረዋል፡፡ የመኖር ዋስትናቸው አደጋ ላይ በመውደቁም ተቆርቋሪ ወገኖች ህይወታቸውን እንዲታደጉላቸው ተማፅነዋል፡፡