እውቁ የብእር ሰው የስነፁሁፋ ገበሬ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል

የስነፁሁፋ ገበሬ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል

ህዳር 3 ቀን 1991 ታላቁ የስነጹሁፍ ሰው ያረፋበት ቀን !!!

በኢትዮጲያ አቆጣጠር ጥቅምት 3 ቀን 1909 ዓ.ም የተወለዱት ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ትምህርታቸውን ገና ልጅ ሳሉ ነበር መከታተል የጀመሩት ፤በመጀመሪያ የአብነት ትምህርታቸውን ቀጥሎም የዘመናዊውን ትምህርታቸውን የመማሩ እድል ገጥሟቸዋል ።

እውቁ የብእር ሰው ከበደ ሚካኤል የጋዜጠኝነት ሞያን ጨምሮ በተለያዮ የመንግስት የሀላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ለሀገራቸው ከፍተኛ ግልጋሎትን ሰጥተዋል፤ ለአብነት ያህልም.. …በትምህርት ሚኒስቴር ፣በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣በፓስታ ቤት ፣በብሔራዊ ቤተመጽሀፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ.. ….ሀላፊ በነበሩበት ዘመን ተጨባጭ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት ችለዋል ።

ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ከ30 በላይ ጽሁፎችን እንደጻፋ ይነገርላቸዋል ከነዚህ ውስጥ የግጥም መድብል፣መጽሀፍቶችና እና ተውኔቶች ይገኙበታል ።
* በላይነህ
*የትንቢት ቀጠሮ
*ታሪክና ምሳሌ
* የቅኔ አዝመራ
* የድርሰት ትንሳኤ
* ታላላቅ ሰዎች
* የስልጣኔ አየር
* አኒባል
* ጃፓን እንደምን ሰለጠነች

ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ህይወታቸው ያለፈው ህዳር 3 ቀን 1991 ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል ።

ኢዮብ ዘለቀ