ገበጣ የኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ባህላዊ ጨዋታ በኮምፒተር ጌም ተፈለሰፈ

VOA : ቅኔ ቴክኖሎጂስ የእጅ ስልኮች እና ኮምፒተሮች ላይ ጨዋታዎችን የሚያመርት ድርጅት ነው።ከዚህ ቀደም አኳኩሉ የተሰኘ ጨዋታ ፈጥሯል።

በቅርቡ ደግሞ ከኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ባህላዊ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነውን የገበጣን ጨዋታ ወደ ኮምፒተር ላይ ጨዋታ ቀይሮ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ዳዊት አብርሃም መሰል ጨዋታዎች የኢትዮጵያዊያንን ባህል እና ትውፊት በዘመነኛ መንገድ ለማስተዋወቅ ያላቸውን ፋይዳ ያነሳሳል።