የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካል የሆነው የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካል የሆነው የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ካሳ እንደገለፁት፥ ቀደም ሲል ከ14 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የድንጋይ ጥቅጥቅ ሙሊት ስራ ተከናውኗል።

ከኮርቻ ግድቡ ቀሪ ስራዎች መካከል 30 ሳንቲ ሜትር ሙሊት ይፈልግ የነበረው የላይኛው አርማታ ሙሊት (ፌስ ስላብ) ስራ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁንም ገልፀዋል።

ይህም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎች መካከል አንዱ ወሳኝ ስራ መጠናቀቁን እንደሚያሳይ አስታውቅዋል።

በኮርቻ ግድብና በዋናው ግድብ ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ስራ የኮርቻ ግድቡ በመጠናቀቁ ዋናውን ግድብ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አቶ በላቸው ተናግረዋል።

ኮርቻ ግድቡ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር ቁመት ያለው መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Image may contain: sky, mountain, ocean, outdoor, nature and water