የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት አንዣቧል ተባለ

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ስር ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች (የፌደራል ተቋማት) የተማሪዎች ደህንነት አደጋ ላይ ሳይወድቅ የመከላከል፣ ተማሪዎችም በሄዱበት ዩኒቨርሲቲ ስጋት ሳያድርባቸው እንደሚሩ የማድረግ የመንግስት ኃላፊነት ነው!

ዛሬም እንደትላንቱ ተማሪዎች ስጋት ላይ ነን፣ በማህበራዊ ሚዲያ በሚናፈሰው ወሬ፣ በየግቢያችን ውስጥ እነማን እደሆኑ በማይታወቁ ሰዎች በሚለጠፉ መልዕክቶች ተሸብረናል በዚህም ግቢያችንን ለቀን በየቤተ እምነቱ ለማደር ተገደናል፣ ምንም በማናውቀው ጉዳይ እየተገላታን ነው ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

በተለይም የጅማ፣ መደወላቡ፣ ሃረማያ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ሁኔታዎች ጥሩ አይደሉም፣ የሚናፈሰውም ወሬ እንቅልፍ የሚነሳ ነው፣ በተቋማቱ ስጋት አንዣቧል ሲሉ መልዕክታቸውን እያደረሱ ይገኛሉ። ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ድርጊት ጋር ተያይዞ በሌሎች ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች ተነሳሳተው ከገዛ ወንድማቸው ጋር እንዲጣሉ፣ እንዲተላለቁም ከፍተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተሰርቷል ብለዋል። ለሁሉም ነገር ሰላም ቀዳሚ ነው ያሉት ተማሪዎቹ መንግስት ደህንነታችንን ማስጠበቅ ከተሳነው በሰላም ወደየቤታችን ይሸኘን ሲሉ ጠይቀዋል።

አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች የወልዲያው ክስተት እንዳሳዘናቸውና በማንም ምስኪን ተማሪ ላይ ይህን መሰሉ ድርጊት ሊፈፀም እንደማይገባ ተናግረው ነገር ግን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች እነሱ ባላደረጉት ነገር ማንነትን መሰረት አድርጎ ማስጨነቅ፣ ማሸበር እና ማሳቀቅ ተገቢ አይደለም ብለዋል። ሁሉም ተማሪዎች ወንድማማች ናቸው በመሃከላቸው ያለውን ስሜታዊነት በማራቅ እርስ በእርስ በመዋደድ እና በመከባበር አብሮ መኖር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

Via TIKVAH-ETH