አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ የዓመቱ ምርጥ የማራቶን ሯጭነት ሽልማት በግሪክ ተቀዳጀ

የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች የዓመቱ ምርጥ የማራቶን ሯጭነት ሽልማት ተቀዳጁ

የአለም ሻምፒዮኖቹ ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ኬንያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች የዓመቱ ምርጥ የማራቶን ሯጭነት ሽልማት ተቀዳጁ።

አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ኬንያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች የአለም አቀፉ የማራቶን እና ረጅም ርቀት ውድድሮች ማህበር የሚያዘጋጀውን የዓመቱ ምርጥ የማራቶን ሯጭነት ሽልማትን ትናንት በግሪክ አቴንስ በተካሄደ ስነ-ስርዓት አሸንፈዋል።

አለም አቀፍ እውቅና ያለው ይህ ሽልማት የተካሄደው ማራቶን በተጀመረባት የግሪኳ ዋና ከተማ አቴንስ ነው።

AIMS የሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ የማራቶን ሯጭነት ሽልማትን ለሰባተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን አትሌቶች ያለፉት 12 ወራት ባሳዩት ምርጥ አቋም ለዚህ ሽልማት እጩ ያደረጋቸዋል ተብሏል።

( IAAF)