በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ተለቀቁ

በጆሐንስበርግ ከተማ ደቡብ አፍሪካ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ተለቀው በፕሪቶሪያ ከተማ በሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

ታዳጊዎች ከወንጀለኞች ነፃ የወጡት በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

Image may contain: 2 people, people smiling, people standing, tree and outdoor

የታዳጊዎች ወላጆችና ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከወንጀለኞች እጅ በሰላም መለቀቃቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹ ሲሆን፣ ኤምባሲው እና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙም ኤምባሲው፤ ከህጻናቱ ቤተሰቦችና ከህብረተሰቡ ጋር በጥምረት ይሰራል ተብሏል፡፡

በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም በዜጎቻችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀለኞችን በህግ ለመፋረድ ለሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ