የምእራብ ኢትዮጵያ ሰላም ማጣት አነጋጋሪ ሆኗል

በምዕራብ ኢትዮጵያ በወለጋ፣ ቤኒሻንል ጉሙዝ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ባለፈው ዓመት ከተከሰተው ግጭት በተጨማሪ በለተይም በአራቱም የወለጋ ዞኖች በታጣቂዎችና የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች መካከል በሚፈጠሩት አለመግባባቶች ምክንያት አካባቢው ለከፍተኛ የጸጥታ ችግር ተጋልጦ ቆይቷል። ይህን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሌሎችም የሚመለከታው አካላት የተለያዩ ውይይቶች እና የሰላም ጉባኤዎች አድርገዋል። ሆኖም ግን በመንገሥት እና በታጣቂዎች መካከል የነበሩ ግጭቶች ዛሬ ላይ አንድ ዓመት ሞላው።

DW : በሰላም እና ደህንነት ላይ ጥናት እያደረጉ የሚገኙ ባለሙያዎች በአካባቢው ለነበረው የጸጥታ ችግር ዋነኛ ምክንያት በመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መካከል የነበረው ስምምነት ግልጽነት የገደለው መሆኑ ነው ይላሉ።

አቶ ኩማ በቀለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና ጸጥታ ጥናት ተቋም የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ይከታተሉ። እንደ አቶ ኩማ ገለጻም በምዕራብ ኢትዮጵያ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ሲካሄዱ የነበሩ የሰላም እና የእርቅ ጉባኤዎች እንዲሁም በኦነግና በመንገሥት መካከል ሲደረጉ የነበሩ ስምምነቶችና ድርደሮች በመተማመን ላይ የተመሰረቱ አይደሉም። ይህ ደግሞ የጸጥታ ችግሩን አባብሶታል ይላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ አካባቢ መንግሥት ሕግን የማስከበር ሥራ ባለመስራቱ ግጭት መበራከቱን እና በቀላሉ ችግሩን ለመፍታት እንዳልተቻለ ይገልጻሉ።

አቶ ሞነኑስ ሁንዳራ ትራብ ሸው ካምበርልጅ በተባለ ተቋም የማኅበራዊ እና ፖለቲካ ዘርፍ አማካሪ እና ተመራማሪ ናቸው። እንደ አቶ ሞነኑስ ገለጻ ደግሞ በወለጋ እና አካባቢው ሰላምን ለማውረድ መንግሥት እና ታጣቂዎች ፍላጎት የላቸውም።

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝም አስተዳደር መምህር የሆኑት ዶክተር ሙሉነህ ካሣ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች ከታጣቂዎች በአካባቢው መኖር በተጨማሪ የወሰን ይገባኛል ውዝግቦችን መኖራቸውን እንደ ምክንያት ያነሳሉ። በተለይም በማኅበራዊ መገናኛ ዜደዎች ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎች በቤኒሻንጉል፣ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮው ለነበረው ግጭት ከፍተኛውን ድርሻ ነበራቸው ይላሉ። ይህን ችግር ለመፍታትም ምከንያታዊ አስተሳሰብን ማዳበር እንዲሁም መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማስከበር አለበት ብለዋል።

በመንገሥት እና ታጣቂዎች መካከል በሚካሄዱ ግጭቶት ምክንያት በነዋሪዎች ላይ ሲደርሱ የነበሩ ጉዳቶችን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችንም የሚታወስ ነው።