የትግራይ ክልል ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ የሚያደርጉት ስደት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ።

DW : የትግራይ ክልል ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ የሚያደርጉት ስደት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ። ክልሉ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ይህ የስደት ጉዳይ ለክልሉ መንግሥት አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ያመለክታል።የክልሉ ሠራተኞና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ዓመት ብቻ 19 ሺህ ዜጎች ከትግራይ ተነስተው ወደ ዓረብና አውሮጳ ሃገራት በሕገወጥ ድንበር አቋርጠው ተጉዘዋል። የወጣቶች ስደት ዋነኛ ምክንያት ሥራ አጥነት መሆኑም ተገልፅዋል። የክልሉ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ይህ የስደት ጉዳይ ለክልሉ መንግሥት አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ያመለክታል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US