መንግሥት ግጭት የሚያነሳሱ አካላትን ከማለባበስ አልፎ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ የሕግ በላይነትን እንዲያረጋግጥ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ጠየቀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ማንም ሰው በማንነቱ የማይሸማቀቅበት ሀገር ለመፍጠር ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ

መንግሥት ግጭት የሚያነሳሱ አካላትን ከማለባበስ አልፎ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ የሕግ በላይነትን እንዲያረጋግጥም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ (አሕፓ) በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በሰጠው መግለጫ ‹‹አሕፓ ለሕግ እና የሕግ የበላይነት ከምንም ነገር አስበልጦ ቅድሚያ የሚሰጥ ፓርቲ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ለተቀጠፈው ሕይወት ችግር ተጠያቂው መንግሥት ነው›› ብሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ ተጠያቂነት እና ፍትሕን ማረጋገጥ አለመቻሉ መሆኑን የፓርቲው የውጭ ግንኙነት እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሳ አደም ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ሆደ ሰፊነት የሚረጋገጠው ሕግን በማስከበር እንጅ አጥፊዎችን በመታገሥ ወደበለጠ ግጭት በመግፋት አለመሆኑንም አሕፓ አስታውቋል፡፡ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ (አሕፓ) የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ዑመር አሊም በመንግሥት ቸልተኝነትና አነሻሾችን በማለባበስ ሠላም እንደማይመጣ ተናግረዋል፡፡

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኮንቴ ሙሳ (ዶክተር) ደግሞ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን መንግሥትን ፕሮፖጋንዳ ላይ መጠመዳቸውን በማቆም እውነትን እንዲዘግቡ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹በአፋር እና ኢሳ ተከስቶ በነበረው ግጭት መነሻው የብሔር ሳይሆን የኮንተሮባንዲስቶች አና ፖለቲከኞች ቅንብር ይበዛዋል›› ያት ዶክተር ኮንቴ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ያልተፈታ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ መኖሩንም አመልክተዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በማስቀደም፣ ሀገር ማለት ሕዝብ በመሆኑ የሀገራችን ሕዝቦች በመፈቃቀር እና በመተባበር ሕዝባዊ አንድነትን በማጠናከርና በማስቀደም ከስሜታዊነት የፀዳ የአብሮነት ገመዳችንን ማጥበቅ አለብን›› ሲልም አሕፓ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 (አብመድ)