ከመንግሥት ጋራ የሚደረገው ውይይት ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና የሚያረጋግጥ ሊኾን ይገባል፤ “ለቋሚ ስጋታችን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ውል ላይ መደረስ አለበት”

መግለጫውን ከውይይቱ በኋላ ለመስጠት ታስቦአል፤ ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶች ይመደባሉ *** የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ከሚመራው የመንግሥት ልኡክ ጋራ የሚያደርገው ውይይት፣ የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ቋሚ የጥቃት እና የተጽዕኖ ዒላማ እየኾነች ለምትገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት የሚደረስበት ሊኾን እንደሚገባው …