ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ ዐወጀ

አገሪቱን ለከፍተኛ ጥፋት እና ድህነት የሚዳርግ እጅግ አሳሳቢ ግጭት እየተስፋፋ ነው፤ የጸጥታ ኀይሎች ቅድመ ግጭትን መሠረት ላደረገ መከላከል ትኩረት እንዲሰጡ ጠየቀ፤ ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭት መንሥኤ ናቸው፤ ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፤ ሶሻል ሚዲያውን ለሰላም፣ አንድነትና ተግባቦት በመጠቀም ኹሉም የበኩሉን ይወጣ፤ *** በአገራችን እንኳንስ ሊደረጉ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሣንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ ክልሎች …