የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለመሥዋዕትነት ሞት እንዲዘጋጁ ፓትርያርኩ አሳሰቡ፤ ምልአተ ጉባኤው የጥቃት መከላከልና የኮሚዩኒኬሽን ኀይለ ግብሮችን እንዲያቋቁም ጠየቁ

“ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቻ ከሰባ ሚሊዮን ያላነሰ ሠራዊት ያለው ጉባኤ እንጂ ብቻውን አይደለም” ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ጀመረ *** በቤተ ክርስቲያን ላይ በቀጣይነት እየደረሰ ያለውን ተጽዕኖ እና ጥቃት ለማስቆም፣ የመንጋው እረኞች የኾኑ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ድምፃቸውን በዓለም ዙሪያ በአንድነት ለማሰማት እና እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት ለመክፈል እንዲዘጋጁ …