ሴክስቶርሽን’Sextortion’ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ቦትኔት መጠነ ሰፊ የኮምፒውተር ቫይረስ ዘመቻ መክፈቱ ተሰማ

ሴክስቶርሽን’Sextortion‘ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ቦትኔት መጠነ ሰፊ የኮምፒውተር ቫይረስ ዘመቻ መክፈቱን የዘርፉ ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡

የመረጃ ጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አካላት በመረጃ ጠላፊዎች የተመዘበረባቸውን ሚስጥራዊ ፎቶግራፎች ይፋ እንዳይወጣባቸው እስከ 800 የአሜሪካን ዶላር በቢትኮይን (Bitcoin) ክፍያ እንደሚጠየቁ ተነግሯል፡፡

ከተጠለፉ መረጃዎች ውስጥ ሚስጥራዊ መረጃዎች አንዱ የተቀባዩ የይለፍ-ቃሎች እንደሚገኝበት ታውቋል፡፡

ጥቃቱ ከ27 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች በተለየ መልኩ ኢላማ ያደረገ ሲሆን በሰዓት እስከ 30ሺህ አጥፊ የኢ-ሜይል መልእክቶች ይሰራጫሉ ተብሏል፡፡

ቦትኔቶች በስርዓተ በኮምፒውተር የበይነ-መረብ ግንኙነቶች ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች እንደሚውሉ የአይቢኤም ሬድ ሴኪዩሪቲ ቡድን (IBM’s X-Force Red security team) የጠቆመ ሲሆን ቦትኔቶች ለህገ-ወጥ ግልጋሎት እንደሚውሉም ገልጿል፡፡

ቦትኔቶች ‘Botnet’ የኮምፐውተር ኔትዎርኮች ሲሆኑ የመረጃ በርባሪዎች ለጥቃት የተጋለጡ የዌብ -ገጾችን እና የኢ-ሜይል አታችመንቶችን በመጠቀም አጥፊ ሶፍትዌሮችን ለማሰራጭት ያውሉታል፡፡

A portion of one typical email sent by the botnet

‘Sextortion botnet spreads 30,000 emails an hour’ . A large-scale “sextortion” campaign is making use of a network of more than 450,000 hijacked computers to send aggressive emails, researchers have warned.

የሳይበር ደህንነት ተቋሙ ቼክ ፖይንት (Check Point) አሁን የተከሰተው የሴክስቶርሽን ጥቃት ፎፒክስ (Phorpiex) ቦትኔትን የሚጠቀም ሲሆን ቦትኔቱ ከአስር አመት በላይ መቆየቱን ገልጿል፡፡

የሳይበር ወንጀለኞች ቦትኔቶችን ለጥቃቱ መጠቀማቸው የሚላኩ ኢ-ሜይል መልእክቶች አላስፈላጊ መልእክቶች (spam) በሚል እንዳይለዩ እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡

የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች በቦትኔቶች አማካኝነት ሊደርሱ የሚችሉ የመረጃ ጥቃቶችን ለመከላከል በአጠቃላይ ሶፍትዌሮችን በተለይ የመረጃ ማፈላለጊያዎችን ማዘመን እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ቼክፖይንት ባደረገው የደህንነት ፍተሻ የመረጃ በርባሪዎቹ በጥቃቱ 11 ቢትኮይን ይህ በገንዘብ ሲሰላ 100 ሺ የአሜሪካን ዶላር ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ መሰብሰባቸውን ጠቁሟል፡፡

ከ450 ሺህ በላይ ኮምወፐውተሮች በቫይረሱ መጠቃታቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

ምንጭ ቢቢሲ – https://www.bbc.com/news/technology-50065713