ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ አጫጭር መልዕክቶችን ለደንበኞች ያለ አግባብና ያለ ፍላጎታቸው የሚልኩትን እንደማይታገስ አስጠነቀቀ።

DW : ኢትዮ ቴሌኮም ከኩባንያው ፈቃድ ወስደው የተለያዩ አጫጭር መልዕክቶችን ለቴሌኮሙ ደንበኞች ያለ አግባብ እና ያለ ፍላጎታቸው የሚልኩትን እንደማይታገስ አስጠነቀቀ። ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶችን ከስልክ ደንበኛው ፍላጎት እና ስምምነት በመነሳት የመረጃ ቅብብል እንዲኖር ፈቃድ ቢወስዱም ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ከዚሁ በተቃራኒ ተሰማርተው በመገኘታቸው ፍቃድ የማቋረጥ ርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ኩባንያው ዐስታውቋል። ደንበኞች የማይፈልጉት መልዕክት ወደ ስልካቸው ከመግባቱም ባለፈ ተስማምተው የጀመሩትን የመረጃ ልውውጥ ስምምነት ማቋረጥ እንደሚቸገሩና ገንዘባቸውም ያለ አግባብ እንደማቀነስባቸው ደጋግመው ይናገራሉ።