" /> እነ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ምርመራ ላይ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

እነ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ምርመራ ላይ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

እነ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ምርመራ ላይ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን በእነ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ምርመራ ላይ የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል።የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እስከ ጥቅምት 12/2012 ዓ.ም ድረስ ክስ እንዲመሠረት ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ቀጠሮ በመስጠት መዝገቡን የዘጋው ፍርድ ቤቱ መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጠርጣሪዎቹ ለ64 ቀናት በማረፊያ ቤት የቆዩ ቢሆንም፣ በእነዚህ ጊዜያት መረጃ እያጣራ ያለመሆኑን፤ ቀሪ ምስክሮችም ጥቂት መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ለጥቅምት 12 ክስ እንዲመሠረት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል።

የፍርድ ሒደቱን ውሳኔ ለመስማት የከተማዋ ወጣቶች ተሰባስበው እየተጠባበቁ ያረፈዱ ሲሆን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱን ተከትሎ ተቃውሞ አሰምተዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ እንደገለፁት ‘ተጠርጣሪዎቹ ይፈቱልን!’ እያሉ በፍርድ ቤቱ አቅራቢያ ተሰባስበው ድምፃቸውን ያሰሙ ቢሆንም ፖሊስ እንደበተናቸው ተናግረዋል።ወጣቶቹን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እንደተጠቀመና የታሰረ ሰው አለመኖሩን ኮማንደሩ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው ‘መፈንቅለ መንግሥት’ ጋር በተያያዘ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወቃል።

BBC Amharic


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV