የአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ፍጥጫ የህይወት መጥፋት እያስከተለ ነው

የአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ፍጥጫ የህይወት መጥፋት እያስከተለ ነው

ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል በርካታ የቀድሞ አመራሮች እና አንዳንድ ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ፅፌ ነበር። ሚድያው ጉዳዩን እየዘገበው ስላልሆነ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ስሞክር ነበር። ዛሬም ይህንን መረጃ ላካፍላችሁ:

የጉዳዩ መነሻ ሶስት አወዛጋቢ ቀበሌዎች የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ስልጣን ላይ እያሉ ወደ አፋር ክልል መካተታቸው ነበር። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ጭምር በተገኙበት ነበር። በቅርቡ ደግሞ የሶማሌ ክልል እነዚህ ቀበሌዎች የእኔ ናቸው ብሎ የካቢኔ ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

በነዚህ ምክንያቶች አካባቢው ሰላም ማግኘት አልቻለም። አሁን ችግሩ ከነዚህ ሶስት ቀበሌዎች አልፎ ሌሎች የሶማሌ ክልል ስፍራዎችን እያዳረሰ ነው። ይህንን እንቅስቃሴ በአፋር በኩል በገንዘብ እና ቁሳቁስ ሲደግፉ የነበሩ ነጋዴዎች እና የቀድሞ አመራሮች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

በሚያሳዝን ሁኔታ ባለፈው ሳምንት ብቻ ብዙ ሰው ህይወቱን አጥቷል። ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች በሶማሌ በኩል 18፣ እንዲሁም በአፋር በኩል ወደ 30 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ይጠቁማሉ!

Elias Meseret


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE