ሰላምና ደኅንነት ከማይፈልጉ አካላት ጋር በድብቅ ትሥሥር አላቸው የተባሉ የወረዳ አስተዳዳሪና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

የአማራ ክልል የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ሁለት የድርጅት ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ለአብመድ በስልክ እንደገለጹት የሥራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ረፋድ ነው፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ የአማራ ክልልን ሰላምና ደኅንነት ከማይፈልጉ አካላት ጋር በድብቅ ትሥሥር አላቸው በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፀጥታ አካላት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አብመድ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE