የቀድሞ የሰገን ዞን ቋሚ የመንግሥት ሠራተኞች አቤቱታ

ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ሀዋሳ የመጡት ሠራተኞች ለዶቼ ቨለ እንዳሉት ዞኑ በፈረሰበት ወቅት ከክልል ጀምሮ በመረጡባቸው ዞኖችና ወረዳዎች እንደሚመደቡ በክልሉ ባለስልጣናት ተገልጾላቸው ነበር። ይሁንእንጂ እስከአሁን የስራ ምደባው አልተሰጣቸውም ፣ ወርሃዊ ደሞዛቸውም ከባለፈው ሐምሌ ጀምሮ ተቋርጦባቸዋል።…