በኦሞ ሸለቆ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሚፈድሙት ግድያ ተበራክቶአል

DW : በኦሞ ሽለቆ ተፋሰስ ላይ በተገነቡ አራት የስኳር ፋብሪካዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ ሰራተኞች የጸጥታ ስጋት ላይ መወደቃቸውን የኢትዮጲያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሰራተኞች ማህበር አስታወቀ። የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ለዶቼ ቨለ ( DW ) እንዳሉት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በፋብሪካዎቹ ሰራተኞች ላይ የሚፈድሙት የግድያ ጥቃት እየተበራከተ መጥቷል። አንደሊቀመንበሩ ገለጻ ታጣቂዎቹ ሰሞኑ ብቻ በተከታታይ በፈጸሙት ጥቃት የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ሾፌርን ጨምሮ በሸንኮራ ማሳ ላይ የተሰማሩ በርካታ ወዛደሮች ለሞትና ለጉዳት ተዳርገዋል። ዶቼ ቨለ (DW )በጉዳዩ ላይ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊን አነጋግሯል።