ለዶ/ር አብይ አህመድ የተበረከተው የሄሰን የሰላም ሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ።

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተበረከተው የሄሰን የሰላም ሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ።

በሄሰን ፌደራዊ ግዛት ዋና ከተማ ቪስባደን በሚገኘው የፌደራል ግዛቱ ምክር ቤት በተከናወነው የሽልማት አስጣጥ ሥነ ሥርዓት የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ሽልማቱን ተቀብለዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሄሰን ፌደራዊ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር የሄሰን ፓርላማ አባላት የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናት የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰላም ሽልማቱ የተሰጣቸው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሰላም ለማውረድ በመቻላቸው መሆኑን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ ያመለክታል።

የሄሰን የሰላም ሽልማት የቦርድ ስራ አመራር እና የሄሰን ፓርላማ ፕሬዝዳንት ቦሪስ ራየን፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአፍሪካ አህጉር ታላቅ ተስፋ ከተጣለባቸው መሪዎች አንዱ ናቸው” ሲሉ አመስግነዋቸዋል።

Image may contain: one or more people and indoor

የሄሰን ፌደራዊ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ፎከር ቡፋየርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ሰላም ካበረከቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ በአፍሪካ ቀንድ ግጭቶችን ለማስወገድ የሚያደርጉትን ጥረትም አድንቀዋል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Photo: DW Amharic

Image may contain: 1 person, standing and indoor