በሰንቀሌ ወታደራዊ ካምፕ የታሰሩት ወጣቶች ተፈቱ

በሰንቀሌ ወታደራዊ ካምፕ የታሰሩት ወጣቶች ተፈቱ!!!

በሰንቀሌ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ በጅምላ ታስረው የነበሩት ወጣቶች ከእስር እየተፈቱ ነው። ከምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ቄለም ወለጋ ከመጡት በስተቀር ከሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች የታሰሩት ወጣቶች መፈታታቸው ታውቋል።

ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት አከባቢዎች የመጡት ወጣቶችንም ለመፍታት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የእስረኛ ቤተሰቦች ወጣቶቹን ለመውሰድ የትራንስፖርት መኪና በማሰባሰብ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በዚሁ መሠረት ከምዕራብ ወለጋ ለታሰሩት ወጣቶች የሚያስፈልገው የአውቶቢስ መኪና ብዛት 12 ሲሆን ለምዕራብ ጉጂ 14 እና ለቄለም ወለጋ ደግሞ 12 አውቶብስ መኪኖች እንደሚያስፈልጉ የእስረኛ ቤተሰቦች ገልፀዋል።